1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጠ/ሚኒስትሩ ማብራሪያ

ማክሰኞ፣ የካቲት 15 2014

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከምክር ቤት አባላት ማብራሪያ ሰጡ። ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ጦርነቱን የተሸከመበት አቅም የሚደነቅ ነው ብለዋል።

https://p.dw.com/p/47Q21
Äthiopien Parlament Addis Abeba
ምስል Solomon Muche/DW

ጠ/ሚኒስትሩ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡት ማብራሪያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ጦርነቱን የተሸከመበት አቅም የሚደነቅ ነው አሉ። ኢትዮጵያ በጦርነት ውስጥ ሆናም ቢሆን በግብርና እና ከውጪ የሚገቡ ሸቀጦችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ያደረገችው ጥረት እና የተሰበሰበው ገቢ ከፍተኛ መሆንን በስኬትነት አንስተዋል። ቂም እና ሌብነት የኢትዮጵያ የዘመናት የቁልቁለት ጉዞ ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸውን የተናገሩት ዐቢይ ዘላቂ ሰላም ለመገንባት ሲባል የሕወሓት ከፍተኛ አመራር የነበሩ ሰዎች ክሳቸው እንዲቋረጥ መደረጉን ተናግረዋል። አክለውም እስካሁን ከሕወሓት ጋር የተደረገ ድርድር የለም፤ ይህ ማለት ግን ድርድር አይኖርም ማለት አይደለምም ነው ያሉት።

ሰሎሞን ሙጬ 

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ