በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የው/ጉ/ሚ ቃል አቀባይ መግለጫ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 6 2014ማስታወቂያ
በትግራይ ክልል እና በፌዴራል መንግሥት መካከል ሰላም እንዲወርድ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙትን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆን የሥራ ሂደትን በተመለከተ በተጨባጭ እዚህ ላይ ደርሰዋል ለማለት እንደማይቻል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ልዩ ልዑኩ ግን የሰላም ጥረታቸውን ቀጥለዋል ተብሏል። ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት በጉዳይ ፈፃሚ ደረጃ ለማስቀጠል መወሰኗ የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ችግር እንዳለው አያመለክትም ሲሉ የሚኒስቴሩ ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል። መንግሥት በሳውዲ አረቢያ በስቃይና በችግር ውስጥ ከሚገኙ ዜጎች መካከል ከሰባት ሺህ የሚበልጡትን ኢትዮጵያዊያን በሳምንት ለሦስት ቀናት ፣ በቀን ሦስት ጊዜ በሚደረግ በረራ መመለሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ይኽ ሥራውም ይቀጥላል ተብሏል።
ሰሎሞን ሙጬ
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ