1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኮንጎ የጣሊያን አምባሳደር ተገደሉ

ሰኞ፣ የካቲት 15 2013

ሁለት የጣሊያን ዜጎች በምሥራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ግዛት ውስጥ መገደላቸውን የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመለከተ። የአውሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ቃል አቀባይ ናቢላ ማስራሊ ሕብረቱ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ለሕብረቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊዎች ዛሬ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3pilv
DR Kongo Krankenhaus Level III Indian Field in Goma
ምስል Djaffar Al-Katany /REUTERS

ሁለት የጣሊያን ዜጎች በምሥራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ግዛት ውስጥ መገደላቸውን የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመለከተ። በዴሞክራቲክ ኮንጎ የጣሊያን አምባሳደር ሉቻ አትናሲዮ እና አንድ የጣሊያን ፖሊስ መኮንን ጎማ ከተማ ውስጥ በተመድ አጀብ በመጓዝ ላይ ሳሉ መገደላቸውን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ይፋ ባደረገው አጭር መግለጫ አረጋግጧል። የጣሊያን ፕሬዝደንት ግድያውን የፈሪ ድርጊት በማለት አውግዘዋል። የአውሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ቃል አቀባይ ናቢላ ማስራሊ ሕብረቱ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ለሕብረቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊዎች ዛሬ ተናግረዋል።«በተመድ አጀብ ላይ ጥቃት መድረሱንና የጣሊያን አምባሳደርን መገደልን የሚያመለክተውን ዘገባ አይተናል። ዜናዎቹ በጣም አሳሳቢዎች ናቸው፤ በመሆኑንም DRC ካለው የሕብረቱ ተልዕኮ ጋር በመሆን በቅርበት እየተከታተልን ነው።» አያይዘውም የአውሮጳ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል ለሮምና ለተመድ የሀዘን መግለጫ ማስተላለፋቸውንም ገልጸዋል።

 

ሸዋዬ ለገሰ

አዜብ ታደሰ