በካን የፊልም ፌስቲቫል ደምቃ የታየችው ኢትዮጵያዊት
እሑድ፣ ሰኔ 3 2010ማስታወቂያ
ባለፈው ግንቦት ወር በፈረንሳይ በተካሔደው የካን የፊልም ፌስቲቫል ከዝነኛ የፊልም ባለሙያዎች ጎን በቀይ ምንጣፍ ላይ የታየችው ዮርዳኖስ ሽፈራው ቀልብ ስባ ነበር። ዮርዳኖስ በመርኃ-ግብሩ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሚታወቀውን ጥበብ ቀሚስ ለብሳ ታይታለች። ዮርዳኖስ በካን የተገኘችው ካፋርናም በተባለ ፊልም ላይ በትወና በመሳተፏ ነበር። ዮርዳኖስ ነዋሪነቷ በዮርዳኖስ ሲሆን በቤት ሰራተኝነት ትሰራለች። ዮርዳኖስ በፊልሙ የተጫወተጫት ገጸ-ባሕሪ የገጠማት ውጣ ውረድ ያለፈችበት ፈተና በእውነተኛ ሕይወቷ እንደሆነ እያለቀሰች ለጋዜጠኞች ተናግራለች። ዮርዳኖስ የተወነችበት ካፋርናም የተባለው ፊልም በፈረንሳይ አገር በሚካሔደው የካን ፊልም ፌስቲቫል ሽልማት አግኝቷል። በዛሬው መሰናዶ ሐይማኖት ጥሩነህ አነጋግራታለች።
ሐይማኖት ጥሩነህ
ኂሩት መለሰ