1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦነግ አመራሮች ውዝግብና የምርጫ ቦርድ ውሳኔ

ረቡዕ፣ መጋቢት 21 2014

ቦርዱ ውሳኔውን ያሳለፈው በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው የፓርቲው አንደኛ የአመራር ክንፍ አምና መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ላካሄደው ጠቅላላ ጉባኤው እውቅና በመንፈግ ነው፡፡ በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የፓርቲው የአመራር ቡድን የቦርዱን ውሳኔ እንደሚቀበል ሲያስታውቅ ሌላኛው ቡድን ግን አሁንም ጉዳዩን በሕግ ለመከታተል እንደሚገደድ ገልጿል፡፡ 

https://p.dw.com/p/49ExV
 Logo Oromo Liberation Front

የኦነግ አመራሮች ውዝግብና የምርጫ ቦርድ ውሳኔ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የአመራሮችን ውዝግብ ለመፍታት ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ ሲል እንደ መፍትሄ አስቀመጠ፡፡ ቦርዱ ይህን ውሳኔ ያስተላለፈው በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው የፓርቲው አንደኛ የአመራር ክንፍ አምና መጋቢት 04 ቀን 2013 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባኤው እውቅና በመንፈግ ነው፡፡ በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የፓርቲው የአመራር ቡድን የቦርዱን ውሳኔ እንደሚቀበል ሲያስታውቅ ሌላኛው ቡድን ግን አሁንም ጉዳዩን በሕግ ለመከታተል እንደሚገደድ ገልጿል፡፡ 
ዘጋቢያችን ሥዩም ጌቱ ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል፡፡
ስዩም ጌቱ 
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ