1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ

ረቡዕ፣ ግንቦት 11 2013

በእነ አቶ ጀዋር መሐመድ የክስ መዝገብ የምስክሮችን ቃል የመስማት ሂደት ላይ ዛሬ ያስቻለው የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በስር ፍርድቤት እንዲታይ ዳግም እንዲታይ ሲል ብይን ሰጠ። ከሳሽ አቃቤ ህግ ከዚህ ቀደም “የምስክሮቼ ቃል ከመጋረጃ ጀርባ በዝግ ችሎት የይደመጥልኝ” ማመልከቻ ውድቅ በመደረጉ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድቤትን ይግባኝ ጠይቆ ነበር።

https://p.dw.com/p/3tctp
Symbolbild Gericht Gesetz Waage und Hammer
ምስል Fotolia/Sebastian Duda

የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ

በእነ አቶ ጀዋር መሐመድ የክስ መዝገብ የምስክሮችን ቃል የመስማት ሂደት ላይ ዛሬ ያስቻለው የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በስር ፍርድቤት እንዲታይ ዳግም እንዲታይ ሲል ብይን ሰጠ። ከሳሽ አቃቤ ህግ ከዚህ ቀደም ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ያቀረበው “የምስክሮቼ ቃል ከመጋረጃ ጀርባ በዝግ ችሎት የይደመጥልኝ” ማመልከቻ ውድቅ በመደረጉ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድቤትን ይግባን በመጠየቁ ነበር የዛሬው ችሎት የተሰየመው። ችሎቱም የተከሻሾች ጠበቆች እና አቃቤ ህግን በጉዳዩ ላይ ሲያከራክር ቆይቶ ዛሬ በሰጠው ብይን አቃቤ ህግ በቅሬታው እና በማመልከቻው ላይ ተጨማሪ ማስረጃዎችን እንዲያጠናክር እና ጉዳዩ እንደገና በስር ፍርድ ቤት እንዲታይ ሲል የወሰነው፡፡

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሀመድ