በእነ እስክንድር ነጋ ላይ ምስክር በግልጽ ችሎት እንዲቀርብ ተወሰነ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 22 2013ማስታወቂያ
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የጸረ ሽብር እና ሕገ መንግስታዊ ወንጀሎች ችሎት በእነእስክንድር ነጋ መዝገብ የተከሰሱ አራት የባልደራስ አባላት ምስክር የመስማት ሂደት በግልጽ ችሎት እንዲታይ ወሰነ። ከተከሳሽ ጠበቆች አንዱ ለዶይቼ ቬለ እንደገለጹት ፍርድ ቤቱ በሰጠው ተለዋጭ ቀጠሮ ዐቃቤ ሕግ ተጨማሪ ምክንያት ሳያቀርብ እና ተከሳሾች ሳይጉላሉ ብይን እንደሚሰጥ ተስፋቸውን ገልጸዋል። ችሎቱ በዛሬው ውሎው በቀጣይ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ከሐምሌ 8 እስከ 16 ባሉ ቀናት ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
ዮሐንስ ገብረግዚአብሔር
ታምራት ዲንሳ
ነጋሽ መሐመድ