1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሳይንስአፍሪቃ

በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ባለሁለት እግር ተሽከርካሪዎች

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 27 2014

ጀርመን ውስጥ የተለያዩ የህዝብና የግል መጓጓዣ አማራጮች አሉ። ሰዎችንና ምርቶችን የሚያጓጉዙ ፈጣን ባቡርች፣ የከተማ ቀላል ባቡሮች ፣ አውቶብሶች፣ የተለያዩ አይነት ብስክሌቶች እና ሌሎች አገልግሎት ላይ ይውላሉ። አሁን አሁን ደግሞ የብስክሌት ቅርጽ ኖሯቸው ቆመው የሚነዱ ባለሁለት እግር በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካርዎች እየተዘወተሩ ነው። 

https://p.dw.com/p/458Vn
E-Scooter in der Stadt
ምስል picture alliance/dpa

የኤሌክትሪክ ቢስክሌቶች

በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ባለሁለት እግር ተሽከርካሪዎች

        
ጀርመን ውስጥ የተለያዩ የህዝብና የግል መጓጓዣ አማራጮች አሉ። ሰዎችንና ምርቶችን የሚያጓጉዙ ፈጣን ባቡርች፣ የከተማ ቀላል ባቡሮች ፣ አውቶብሶች፣ የተለያዩ አይነት ብስክሌቶች እና ሌሎች የቴክኖሎጂ ውጤቶች አገልግሎት ላይ ይውላሉ።
አሁን አሁን ደግሞ የብስክሌት ቅርጽ ኖሯቸው ቆመው የሚነዱ ባለሁለት እግር በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካርዎች እየተዘወተሩ ነው። 

መርጋ ዮናስ በዶቸቨለ ለሶስት አመታት በጋዜጠኝነት አገልግሏል። በአሁኑ ሰአት ደግሞ በሚድያና ኮሚዩኒኬሽን የሶስተኛ ዲግሪውን እየተማረ ይገኛል።
መርጋ ኢስኩተር እየተባለች የምትታወቀውን ባለሁለት እግር በቁም የምትነዳ ብስክሌት ተጠቃሚ ነው። 

Deutschland, Köln | E-Scooter
ምስል picture alliance/JOKER

            
ጀርመን ውስጥ የተለያየ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች በየትም ቦታ ተደራሽ ቢሆኑም በነዚህ መጠቀም የማይችል ወይም የማይፈልግ ደግሞ የተለያዩ ቀላል የቴክኖለጂ ውጤቶችን መጠቀም የተለመደ ነው። አሁን አሁን በጀርመን ጎዳናዎች ለነሱና ለብስክሌት በተሰመረው መንገድ ባለሁለት እግር በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ብስክሌቶች ሲርመሰመሱ ማየት የተለመደ ሆነዋል።ስለነዚህ በቁም የሚነዱ የኤሌክትሪክ ብስክሌቶችን በተመለከተ መርጋ ዮናስን ጠይቀነው ልምዱን አጋርቶናል። እነዚህ ባለሁለት እግር የኤሌክትሪክ ብስክሌቶች በተለይ የህዝብ እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው አካባቢዎች እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች ቆመው ይታያሉ። በነዚሀ ብስክሌቶች መጠቀም የሚፈልግ ሰው ለነሱ በተዘጋጀው መተግበሪያ አጠገቡ በቅርብ ርቀት ያሉትን ፈልጎ ያገኛችዋል። በመተግበሪያው ላይ ስም፣ የባንክ አካወንት በተለይ ደግሞ ክረዲት ካርድ ቁጥር ከሞሉ ቦሃል ብስክሌቱ ለአገልግሎት ዝግጁ ይሆናል ሲል መርጋ ዮናስ አጫውቶናል።

Frankreich Coronavirus
ምስል Lewis Joly/AP Photo/picture-alliance

ባለሁለት እግር ተሽከርካሪዎቹ በኤሌክትሪክ ቻርጅ በሚደረግ ባትሪ የሚሰሩ በመሆናቸው  የአየርና ድምጽ ብክለትን ለመቀነስ ተመራጭ ናቸው።

እነዚህን ብስክሌቶች በዋናው የመኪኖች ጎዳና መንዳት አይቻልም። ለነሱና ለብስክሌት ብቻ በተፈቀደ መንገድ መጠቀም ይቻላል።ብስክሌቶቹ በሰአት 20 ኪሎሜትር ብቻ እንዲሄዱ ሆነው የተፈበረኩ ሲሆን እንደየሰዉ ክብደት ፍጥነታችው ከዛ በታች ሊቅንስ ይችላል።

Elektroroller
ምስል DW

ቴክኖሎጂው ለአጠቃቅም ቀላል በመሆኑ በማንኛውም እድሜ ክልል ያለ ሰው እነሱን ተጠቅሞ እለታዊ ስራውን መከወን ይችላል።

        
ባለሁለት እግር የኤሌክትሪክ ብስክሌቶቹን ከተጠቀሙ ቦኋላ ወደነበሩበት የመመለስ ግዴታ የለቦትም። መሄድ የፈለጉበት ቦታ ከደረሱ ቦኋላ ለነሱ አልያም ለብስክሌቶች ተብሎ በተዘጋጀ ቦታ በማስቀመጥ መተግበርያውን ከፍተው ጉዞዎን መጨረስዎ ማሳወቅ አለብዎት ። መተግበርያው የተጠቀሙበትን ሰአት በማስላት ገንዘቡን ከሂሳብዎ ቀንሶ ይወስዳል በማለት መርጋ ዮናስ ልምዱን አካፍሎናል።

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር

ነጋሽ መሃመድ