1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«በኢትዮጵያዊነቴ እኮራለሁ» ዮሴፍ ክሮንፍሊ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 7 2012

ኢትዮጵያዊን አይቼ ማለፍ አልችልም። ታዲያ በስራዬ ወደተለያዩ ዓለማት ስሄድ የምፈልገዉ የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግቤት ነዉ። ኢትዮጵያዊ ስለማልመስል ድንገት በአማርኛ ሳወራ በጣም ይደነግጣሉ። ከዝያም በደስታ ያናግሩኛል።

https://p.dw.com/p/3gvj0
Deutschland Joseph Kronfli  der Geschäftsführer Nürnberger Baugruppe
ምስል Joseph Kronfli

ኢትዮጵያዉያን እርስ በራሳችን ካልተከባበርን ማንም አያከብረንም

ዮሴፍ ክሮንፍሊ ይባላሉ። በጀርመን የተለያዩ የመኖርያ ቤቶችን እና ግዙፍ ሕንጻዎችን መንገዶችን ድልድዮችን ብሎም ከሕንጻ ጋር የተገናኘ የኤንፎርሚሽን ቴክኒክ «IT» ን የሚነግድ የአንድ ግዙፍ ኩባንያ ዋና ተጠሪ ናቸዉ። በተለያዩ የጀርመን ከተሞች በሚገኘዉ በዚህ ኮባንያ ስር የሚገኙ 10 ቅርንጫፍ ኩባንያዎችን በስራቸዉ ያስተዳድራሉ። ዮሴፍ በኢትዮጵያዊነቴ የምኮራ ኢትዮጵያን በሄድኩበት ሁሉ የምፍለግ ነኝ ሲሉ ስለኢትዮጵያ ያላቸዉን ፍቅር ይገልፃሉ። ይህን ሲሉ ለሥራ በሄዱበት የዓለም ጫፍ  ሁሉ በእረፍት ጊዜያቸዉ የሚፈልጉት ኢትዮጵያን የሚያስታዉሳቸዉን የኢትዮጵያዉያንን የባህል ምግብ ቤት ነዉ።  ሶርያዊዉ የአቶ ዩሴፍ ክሮንፍሊ አባት ኑሮአቸዉን በሱዳን ካርቱም ያደረጉ ግብጽ ሁሉ ድረስ የሚታወቁ ነጋዴ ነበሩ። በካርቱምም «ጎርደን» የሚባል ታዋቂ ሆቴል ነበራቸዉ። የዝያን ግዜዉን የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ኃይለሥላሴ በግዞት በነበሩበት ከእንጊሊዝ ወደ ሃገራቸዉ ሲመለሱ በሱዳን በማቋረጣቸዉ መዲና ካርቱም ጎርደን ሆቴል በሚባለዉ በሶርያዊዉ የዮሴፍ አባት ታዋቂ ሆቴል ዉስጥ ነበር ያረፉት ።  ጃንሆይ ሶርያዊዉን የሆቴል ባለቤት የአቶ ዮሴፍን አባት ተዋዉቀዉ ወደ ኢትዮጵያ  ይጋብዙዋቸዋል። የዮሴፍ አባት ወደ ኢትዮጵያ በግብዣ እንደመጡ ጃንሆይ አዲስ አበባ ሆቴል እንዲያቋቁሙላቸዉ  ይጠይቋቸዋል። ከዝያም ነዉ ሶርያዊዉ የአቶ ዮሴፍ አባት ከኢትዮጵያ ጉብኝታቸዉ በተመለሱ ከሁለት ዓመት ግድም በኃላ ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዉ እቴጌ ሆቴልን አሪዞን የተባለ የምግብ ቤት እና የምሽት ክለብ ብሎም ሌሎች ቡና ቤቶችን ያቋቋሙት። አሪዞን የተባለዉ የምሽት ክለብ ክቡር ዘበኛ የሙዚቃ ቡድን ጣዕመ ዜማን በሚያሳይበት መድረክም ዝነኛዉ ሙዚቀኛ ጥላሁን ገሰሰ ፤ ማህሙድ አህመድን ጨምሩ የተለያዩ ሙዚቀኞች እዉቅናን ያገኙበት ቦታ ነዉ።  የአቶ ዮሴፍ አባት አዲስ አበባ ሲኖሩ ታድያ የጣልያን ክልስ የሆነቱን ኢትዮጵያዊትዋን የዮሴፍን እናትን ተዋዉቀዉ ትዳር መሰረቱ ። ዮሴፍም ተወለዱ።  

Äthiopisches Essen
ምስል Joseph Kronfli

አቶ ዮሴፍ ስድስት ዓመት ሞላቸዉ እና በጀርመን ትምህርት ቤት ይገባሉ። 12 ዓመት ሲሞላቸዉ፤ የንጉሱ ዘመን ያበቃና ደርግ ኢትዮጵያን ያስተዳድር ጀመር። ደርግ ስልጣን በተቆናጠጠ በሦስተኛዉ ዓመት ኢትዮጵያዉስጥ የፖለቲካ አለመረጋጋት ይከሰታል ። የዝያን ጊዜ አቶ ዮሴፍ የ15 ዓመት ልጅ ነበሩ ፤ እህትም አለቻቸዉ ። ወደ ጀርመን ተላኩ።  አዳሪ ትምህርት ቤት በጀርመን።  አቶ ዮሴፍ ክሮንፍሊ በሞያዋ የቆዳ ሐኪም ጀርመናዊት ባለቤታቸዉ ጋር የ 22 እና የ 20 ዓመት ወንዶች ልጆች አልዋቸዉ ። ኢትዮጵያ የታላቁ ሕዳሴን ግድብ በመገንባትዋ እንዲሁም የዉኃ ሙሌት በመጀመሩም በጣም ደስተና ናቸዉ። በግንባታዉ ገንዘብን በመስጠት ብዙ ጊዜ ተሳትፈዋል አሁንም ርዳታቸዉን እደቀጠሉ ነዉ።

አቶ ዮሴፍ የትዉልድ ሃገራቸዉ የኢትዮጵያ አንዱ ቋን4 የሆነዉን አማርናን ፤ የአባታቸዉን ሃገር ቋንቋ ፤ አረብኛ፤ እንዲሁም ጣልያንና ጀርመንኛ ፈረንሳይኛን መፃፍ ማንበም በናገር ይችላሉ። የሚዉቁትን ስድስት ቋንቋዎች እንደዉ በመላ ልናገር አማርኛ፤ ጀርመንኛ ፤ እንጊሊዘኛ ፤ ጣልያንኛ፤ ፈረንሳይኛ ስድስተና ምንድን ነዉ። አቶ ዮሴፍ የተበላሸ ባህል ያሉት አለመከባበርን ለኔ ቀይ መስመር ማለፍ ነዉ እሱን አልቀበልም ብለዋል። አቶ ዮሴፍ ክሮንፍሊ ለሰጡን ቃለ-ምልልስ በዶቼ ቬለ ስም በማስገን ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።  

አዜብ ታደሰ