1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የመከሩት የአዉሮጳ ኅብረት ሚኒስትሮች

ማክሰኞ፣ ሰኔ 14 2014

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ፤ በአፍርካ ቀንድ በተለይም በኢትዮጵ ላይ ወሳኝ ውሳኔዎችን ሊያሳልፍ ይችላል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ይሁንና የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት በዓለምአቀፍ ደረጃ የፈጠረው የምግብ ዋስትና ችግርና በጆፖለትካው ላይ የፈጠረው ተጽኖ የስብሰባው ዋና ትኩረት ሁኖ መዋሉ ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/4D0vm
EU I Sanktionen gegen Russland I Josep Borrell
ምስል Jean-Christophe Verhaegen/AP/picture-alliance

በአገሪቱ ያለውን የሰባዊ መብት ሁኒታና የእርድታ ተደራሽነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል

ትናንት በሉክዘምበርግ የተካሄደው የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ፤ በአፍርካ ቀንድ በተለይም በኢትዮጵ ላይ ወሳኝ ውሳኔዎችን ሊያሳልፍ ይችላል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ይሁንና የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት በዓለምአቀፍ ደረጃ የፈጠረው የምግብ ዋስትና ችግርና በጆፖለትካው ላይ የፈጠረው ተጽኖ የስብሰባው ዋና ትኩረት ሁኖ መዋሉ ተገልጿል። የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊና የሰብሰባው መሪ ሚስተር ጆሴፕ ቦሪየል ከስብሰባው በኋላ በሰጡት መግለጫ፤ ሚኒስትሮቹ ዩክሬንን በወታደራዊና በሩሲያ ላይ ጫና በመፍጠር መርዳት የሚያስፈግ መሆኑን በጽኑ እንዳመኑበት አውስተው፤ ይህም ጦርነቱ ከዩክሬን አልፎ በሌሎችም ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል። “ሩሲያ የከፈተችው ጦርነት በዩክሬን ላይ ከፍተኛ ጉዳይ ያደረሰ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ግን ከዚያ አልፎ  በምግብና ነዳጅ ዋጋ መናር መክኒያት የለምን ኢኮኖሚም የሚያናጋ ሁኗል” በማለት ሩሲያ በሁሉም ቦታ እየታየ ላለው የኢኮኖሚ ችግርና የምግብና ነዳጅ ዕጥረት ተጠያቂ መሆኗን አስታውቀዋል።

የአፍርካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የሆኑት የስኔነጋል ፕሬዝዳንት ሚስተር ማኪ ሳል ቀደም ሲል ምዕራባያን በሩሲያ ላይ የጣሉት ማዕቀብ የአፍርካ አገሮች ዕህልና ማዳበሪያ ከሩሲያ እንዳይገዙ አግዷቸዋል፤ በአፍሪካ እየተፈጠረ ላለው የእህል እጥረትና የምግብ ችግር አውሮፓም አስተዋጾ እያድረገ ነው በማለት ህብረቱ ሁኒታውን እንዲያሻሽል አሳስበው ነበር። 

ሚስተር ቦርዬል ግን በመግለጫቸው ለተፈጠረው ችግር ሁሉ ኃላፊነቱን መውሰድ ያለባት ሩሲያ እንጂ ህብረቱና በሩሲያ ላይ የተላለፈው ማእቀብ አለመሆኑን አጠንክረው ነው የገለጹት፤ “ሩሲያ ናት የዩክሬንን የውጭ ንግድ ያገደችው እኛ አይድለንም፤  የዩክሬንን ወደቦች፤ የእህል መጋዝኖችንና የመጓጓዣ መሰረተልማቶችን  እያፈረሰች ያለችው ሩሲያ እንጂ ህብረቱ አይደለም በማለት የዓለም የምግብ ቀውስን ያስከተለው ይህ የሩሲያ እርምጃና ምግብን እንደጦር መሳሪያ የመጠቀም ፖለሊዋ እንጂ የመዕራባውያን ማዕቀብ አለመሆኑን አብራርተዋል።

Bundespräsident Steinmeier in Lettland - Familienfoto der Drei-Meere-Initiative des Gipfeltreffens
ምስል Britta Pedersen/dpa/picture alliance

ይሁንና  ሚስተር ቦርየል የአፍርካ መሪዎች የህብረቱ ማዕቀብ ሊያስክትል በሚችለው ተዛማጅ ችግር ላይ የሚያነሱትን ቅሬታ፤ ሚኒስትሮቹ ያዳመጡ መሆኑን አስታውቀዋል። ለአፍርካ መሪዎችና ለገንዘብ ተቋማትም የህብረቱ ማዕቀብ የሚመለከተው የአውሮፓ ህብረት አገሮችን እንጂ ሌሎችን እንዳልሆነና፤ ማዕቀቡ ከሩሲያ ጋር የሚደረግን የምግብና የማዳበሪያ ግብይትን እንደማያግድ የሚገልጽ ደብዳቤ እንደሚጽፉ አስታውቀዋል። ሚስተር ቦርየል አክለውም የሩሲያው ጦርነት በአካባቢው ሊያስከትል የሚችለውን ጂኢኦ-ፖለቲካዊ ቀውስንና የምግብ ዋስትናን እጥረት በመገንዘብ እርምጃዎችን ለመውሰድ ሚኒስትሮቹ የተስማሙ መሆኑን ገልጸዋል። “ በሳህል ብቻ ያለውን የምግብ ዋስትና ችግር ለመርዳታ 1 ቢሊዮን ኢሮ፣  በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የምግብ ችግር ለመቅረፍ 600 ሚሊዮን ይሮ  እንዲሁም በስሜናዊው ፍርካ ሊከሰት የሚችለውን የምግብ ቀውስ ለመግታት 225 ይሮ ለመለገስ ቃል የተገባ መሆኑን አስታውቀዋል። 

ከሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ጋር ከተያያዙ አጀንዳዎች  ውጭ ሚኒስትሮቹ በስፋት የተወያዩት በአፍርካ ቀንድ በተለይም በኢትዮጳያ ላይ እንደሆነ ሚስተር ቦርየ ተናግረዋል ፡ “በመጨረሻ ሰፊ ውይይት የነበረው በኢትዮጵያ ላይ ነበር። መሻሻሎች ታይተዋል፤ ግን ግንኙነትን ወደነበረበት ለመመለስ  የሚያስችል አይደሉም በማለት ሁኒታውን በጥንቃቄ መከታተል እንደሚይስፈልግና ማናቸውም የሚወሰዱ እርምጃዎችም የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሺነትንና የአገልግሎት ተቁማት መመለሳቸውን ባረጋገጠ ቅድመ ሁኒታ ላይ መመስረት እንዳለባቸው የታምነበት መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጳያ መንግስት የምግብ ተደራሽነትን ለማረጋገጥና ሰላም ለመፍጠር እየወሰዳቸው ያሉትን እርምጃዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ህብረቱ በኢትዮጵያ ላይ የጣላቸውን እገዳዎች እንዲያነሳና ግንኙነታቸው እንዲሻሻል ሲያሳስብ እንደነበረ ሁሉ፤ ሌሎች ደግሞ ለምሳሌ አነደ ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ሂዉማን ራይትስ ዋች የመሳሰሉ የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የሚወስዳቸው የማሻሻያ  እርምጃዎች በአገሪቱ ያለውን የሰባዊ መብት ሁኒታና የእርድታ ተደራሽነትን መነሻ በማድረግ  ብቻ መሆን እንደሚገባው በደብዳቤ ጭምር ሲያሳስቡ ቆይተዋል ። 

የሚኒስትሮቹ ስብሰባ ውሳኔ  ግን የኢትዮጵያ መንግስት እንደጠየቀውም ባይሆን ሌሌሎች ወገኖችም እንደፈለጉት እንዳልሆነና ወደፊት ሁኒታዎችን በቅርበት እየተከታተለ በሚታዩ  መሻሻሎች ልክ ለውጦችን ለማድረግ ፋላጎት የታየበት ነው ተብሏል።

ገበያው ንጉሴ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ