1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ ያለ ዕድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛት

ረቡዕ፣ ነሐሴ 8 2011

ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በነገው ትውልድ ላይ ሰፊ አደጋ «የጋረጠ» ያሉት ይህ ችግር ጊዜ ሊሰጠው እንደማይገባ አሳስበዋል። የሴቶች ግርዛት በስፋት ይካሄድባቸው የነበሩት የአፋርና ከሐረሪ ክልል ተወካዮች፣ በአሁኑ ጊዜ የሴቶች ግርዛት በጣም መቀነሱን ተናግረዋል። በገጠር አካባቢዎች ግን የተፈለገውን ያህል ውጤት አለመገኘቱንም ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3Ntwr
Äthiopien Addis Abeba Bildung und Eliminierung von Kinderehen
ምስል DW/Getachew Tedla

ሴቶች እና ሕናት ላይ የሚደርሱ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ጨርሶ ለማስቆም የተቀረጸው ፍኖተ ካርታ

በኢትዮጵያ ሴቶች እና ሕናት ላይ የሚደርሱ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ጨርሶ ለማስቆም የተቀረጸው ፍኖተ ካርታ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ይፋ የሆነ። በስነስርዓቱ ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በነገው ትውልድ ላይ ሰፊ አደጋ «የጋረጠ» ያሉት ይህ ችግር ጊዜ ሊሰጠው እንደማይገባ አሳስበዋል።የሴቶች ግርዛት በስፋት ይካሄድባቸው የነበሩት የአፋር እና ከሐረሪ ክልል ተወካዮች፣ በአሁኑ ጊዜ የሴቶች ግርዛት በጣም መቀነሱን ተናግረዋል።በገጠር አካባቢዎች ግን የተፈለገውን ያህል ውጤት አለመገኘቱንም ገልጸዋል።የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ