የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት
ዓርብ፣ መጋቢት 28 2010ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ለወራት ተቋርጦ የቆየው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ዛሬ ከሰዓት በኋላ መጀመሩን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ ተጠቃሚዎች ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ተጠቃሚዎቹ በድምጽ እና በጽሔፍ በዋትስ አፕ እና በፊስቡክ ባስተላለፉት መልዕክት አገልግሎቱ መቀጠሉን ግን አረጋግጠውልናል። በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ኢንትርኔት አልፎ አልፎ እንደሚቆራረጥ እና ፍጥነትም እንደሌለው የተናገሩም አሉ። በአካባቢያችን የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ገና አልተጀመረም ያሉንም አሉ።
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ