1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች የዉጭ ጉዳይ ሚ/ር መግለጫ

ዓርብ፣ ኅዳር 11 2013

በስድስት የምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት የተደረገዉና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራዉ የልዑክ ቡድን የጠ/ሚ ዐብይ አሕመድን መልክት ያደረሰ፤ ብሎም በሰሜን ኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለዉን ሕግ የማስከበር ተግባር ለጎረቤት ሃገራት ያስገነዘበ ነበር ተብሏል።

https://p.dw.com/p/3lcEY
Tigray-Konflikt | Äthiopien PK Regierungssprecher Dina Mufti
ምስል Solomon Muchie/DW

«ሁሉም የሃገራት ችግሩ የዉስጥ ጉዳይ ነዉ የሚል አንድ አቋም ነዉ ያላቸዉ»


በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራው የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጉብኝት ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል እያከናወነችው ላለው ሕግ የማስከበር ተግባር ለጎረቤት ሀገራቱ ጥሩ ግንዛቤ የተፈጠረበት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ሀገራቱ ጉዳዩ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን፣ ጣልቃ እንደማይገቡና ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ የሰላም ምሰሶ መሆኗን ያረጋገጡበት ነበር ብሏል። በሱዳን በኩል ሸሽተው የተሰደዱ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስም ሱዳን ትብብር እንደምታደርግ ማሳወቋም በመግለጫው ተነግራል። የግብፅና የሱዳን የጋራ ወታደራዊ ልምምድን በተመለከተም የሁለቱ ሀገራት ልምምድ በኢትዮጵያ ኪሳራ እንደማይሆን ኢትዮጵያ እንደምታምንና ሱዳንም ደቡብ ሱዳንም ይህንን እንደሚያራምዱ ለኢትዮጵያ ማረጋገጣቸው በመግለጫው ተገልጿል።

ሰለሞን ሙጬ 

አዜብ ታደሰ 
ኂሩት መለሰ