1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ኹኔታ ላይ የተደረገ ውይይት 

እሑድ፣ ኅዳር 13 2013

በውይይቱ በምኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ዶክተር ቢቂላ ሑሪሳ፣ የፖለቲካ ተንታኙ ዶክተር አደም ካሴ፣ የግጭት ትንተና እና አፈታት ባለሙያው አቶ ዓለማየሁ ፈንታው እና በሐንጋሪ ብሔራዊ የፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በሕዝብ አስተዳደር የዶክትሬት ዲግሪያቸውን እያጠኑ የሚገኙት አቶ ታከለ በቀለ ተሳትፈዋል።

https://p.dw.com/p/3lg2T
Tigray-Konflikt | Äthiopisches Militär
ምስል Ethiopian News Agency/AP/picture alliance

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ኹኔታ ላይ የተደረገ ውይይት 

በኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና በህወሓት ታማኝ ኃይሎች መካከል ውጊያ ከተቀሰቀሰ ሶስተኛ ሳምንታት አስቆጠረ። ይኸ ውጊያ የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ያስከትላል የሚል ሥጋት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ይሰማል። ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ዕኩለ ለሊት በተጀመረው ውጊያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተገድለዋል፤ ከ30 ሺሕ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል። ሊፈጥር ከሚችለው ማህበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ቀውስ ባሻገር በኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ላይ በአገሪቱ ሕልውና ላይ ምን ተፅዕኖ ያሳድራል?

በውይይቱ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ምኒስትር ጽህፈት ቤት በምኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ዶክተር ቢቂላ ሑሪሳ፣ የሕገ-መንግሥታዊ ዴሞክራሲ እና የአስተዳደር ጉዳዮች አማካሪ እና የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት ዶክተር አደም ካሴ፣ የግጭት ትንተና እና አፈታት ባለሙያው አቶ ዓለማየሁ ፈንታው እና በሐንጋሪ ብሔራዊ የፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በሕዝብ አስተዳደር የዶክትሬት ዲግሪያቸውን እያጠኑ የሚገኙት አቶ ታከለ በቀለ ተሳትፈዋል። ይኸ ውይይት የተደረገው አርብ ሕዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ነው። 

ውይይቱን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ

እሸቴ በቀለ