1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ ሰላማዊ ፖለቲካ እንዴት ሊሰፍን ይችላል?

እሑድ፣ ጥር 9 2013

መንግሥት ሕግ ማስከበር በሚለው በትግራዩ ዘመቻም ከመንግሥትም ከሕወሓት ኃይሎችም በኩል  የሞቱ የቆሰሉና የተፈናቀሉት በርካቶች ናቸው።ጦርነቱ ጋብ ካለ በኋላ መንግሥት ጁንታ የሚላቸው የወያኔ ሐርነት ትግራይ(ህወሓት)መሥራቾችን ጨምሮ የፓርቲው አመራራሮችና ሌሎችም አባላት መገደላቸውን በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና መማረካቸውንም ይፋ እያደረገ ነው።

https://p.dw.com/p/3nzff
Karte Äthiopien englisch

እንወያይ፦ በኢትዮጵያ ሰላማዊ ፖለቲካ እንዴት ሊሰፍን ይችላል?

 

በኢትዮጵያ ካለፈው ሁለት ዓመት ተኩል ወዲህ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የበርካታ ሰዎች ሕይወት የጠፋባቸው ብዙ ንብረትም የወደመባቸው ግጭቶች ተካሂደዋል።የሰዎች ግድያና መፈናቀል አሁንም በተለይ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልና በምዕራብ ኦሮምያ እንደቀጠለ ነው።መንግሥት ሕግ ማስከበር ባለው በትግራዩ ዘመቻም ከመንግሥትም ከሕወሓት ኃይሎችም በኩል  የሞቱ የቆሰሉና የተፈናቀሉት በርካቶች ናቸው።ጦርነቱ ጋብ ካለ በኋላ መንግሥት ጁንታ የሚላቸው የወያኔ ሐርነት ትግራይ(ህወሓት)መሥራቾችን ጨምሮ የፓርቲው አመራራሮችና ሌሎችም አባላት መገደላቸውን በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና መማረካቸውንም ይፋ እያደረገ ነው።በመንግሥት መግለጫ መሠረት ከተገደሉት ውስጥ የህወሓት መሥራቾች አቶ ስዩም መስፍንና አባይ ፀሐየ፤ በቁጥጥር ስር ከዋሉት የፓርቲው አመራሮች መካከል ደግሞ የፓርቲው የረዥም ጊዜ መሪ አቶ ስብሀት ነጋና የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት አባይ ወልዱን ጨምሮ ሌሎች አባላት ይገኙበታል።የትግራዩ ጦርነትና አስተምህሮቱ እንዲሁም ሰላማዊ ፖለቲካ በኢትዮጵያ እንዴት ማስፈን ይቻላል? የዛሬው እንወያይ የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ናቸው። በውይይቱ ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ የፖለቲካ ሳይንስና የሕግ ምሁር ከጀርመን፤ አቶ ቴዎድሮስ ዘውዱ በቶሮንቶ ዮርክ ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪና በቅይጥ ማንነት ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡ የማኅበረሰብ ጥናት ባለሞያ እንዲሁም ጋዜጠኛ የትነበርክ ታደለ ተሳትፈዋል።ሙሉውን ውይይት ለማዳመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ኂሩት መለሰ