1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ ሥጋት የደቀነዉ የበረሃ አንበጣ

ማክሰኞ፣ ጥር 26 2012

የአንበጣ መንጋው ከሶማሊያ በአምስት አቅጣጫ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ሸሽቶ የነበረው ዳግም ወደ ኢትዮጵያ እየተመለሳ ሲሆን ይህም ስጋቱን የበለጠ እንዳናረውና በቀጣይም ለአንበጣው መዛመት ምቹ የአየር ንብረት የሚያገኝ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገልፆአል።

https://p.dw.com/p/3XGEA
Kenia Heuschreckenplage
ምስል picture-alliance/AP Photo/B. Curtis

ለአንበጣው መዛመት ምቹ የአየር ጠባይ እየመጣ ነዉ

መቀመጫውን አዲስ አበባ ካደረገው የምስራቅ አፍሪቃ የበረሃ አንበጣ መከላከያ ድርጅት የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በምስራቅ አፍሪቃ ሦስት የአንበጣ አይነቶች ይገኛሉ። እነዚህም የበረሃ ፣ የአፍሪቃ ተዛማጅ እና የዛፍ የሚል መጠርያ አላቸዉ።

አሁን ላይ በቀጣናው የተከሰተው የበረሃ አንበጣ ሲሆን በኢትዮጵያም ከ ሰኔ ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ ተከስቷል። መንጋው ከሶማሊያ በአምስት አቅጣጫ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ሸሽቶ የነበረው ዳግም ወደ ኢትዮጵያ እየተመለሳ ሲሆን ይህም ስጋቱን የበለጠ እንዳናረውና በቀጣይም ለአንበጣው መዛመት ምቹ የአየር ንብረት የሚያገኝ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገልፆአል።

Infografik Heuschreckenplage Afrika Asien EN

የመከላከል ስራው ከባህላዊ ባሻገር ከውጪ በክራይ በገቡ ሦስት አውሮፕላኖች የኬሚካል ርጭት እየተደረገ ነው። ያም ሆኖ የአንበጣው መንጋ የሚያርፍባቸው አካባቢዎች ተራራማና በረሃማ በመሆናቸው ስራውን ማክበዱን ነው ለማወቅ የተቻለው።

Kenia Heuschreckenplage
ምስል picture-alliance/AP Photo/B. Curtis

የአንበጣው መንጋ እስካሁን ያደረሰው የጉዳት መጠን በሁለት አቅጣጫ መጠናቱንና ውጤቱም በሂደት ይገለጻል ተብሏል። ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ እዚያው ከተማው ላይ የተፈለፈለና ያደገ ሳይሆን ከኬሚካል ርጭት ያመለጠ እና ይህን ያህል ስጋት ዉስጥ የሚከት አይደለም ተብሏ።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ