በኢራን የቀጠለው ተቃውሞ እና ዓለም አቀፉ ማኅበረ-ሰብ
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 30 2010ማስታወቂያ
እስካሁን ድረስ በተቃውሞው 24 ሰዎች መመሞታቸውን፣ በርካቶች መቁሰላቸውን እና ከ450 በላይ ተቃዋሚዎች ታፍሰው እንደታሰሩ የዜና ወኪሎች ዘግበዋል።ለኢራን ችግር መፍትሄ ካልተገኘ ችግሩ ተባብሶ የመካከለኛው ምስራቅን እና የተቀረውንም አከባቢም ያናጋል ተብሎ ተፈርቷል። ሆኖም በኢራን በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት እንዲወያይ አሜሪካ ሀሳቡን ስታቀርብ ተቃውሞ ቀርቦባታል። ቻይና ውይይቱን “በኢራን የውስጥ ጉዳይ መፈትፈት” ስትል ጠርታዋለች። ተአቅቧቸውን ካሳዩ ሶስት ሀገራት መካከል ደግሞ አንዷ ኢትዮጵያ ነበረች።
ማትያስ ፎን ሀይነ/ይልማ ኃይለሚካኤል
አርያም ተክሌ