በአፋር ክልል ፓርቲዎች ምርጫዉ በድጋሚ ይካሄድ አሉ
ሰኞ፣ ሰኔ 28 2013ማስታወቂያ
በአፋር ክልል የተካሄደዉ ምርጫ የምርጫን መስፈርት ስለማያሟላ ድጋሚ መካሄድ አለበት በሚል አቋማቸዉ እንደፀኑ አምስት በአፋር ክልል የተወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ። የፓርቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ይፋ ባደረጉት የፅሁፍ መግለጫ እና ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸዉ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ከዚህ ቀደም በአፋር ክልል ፓርቲዎች የጋራ መድረክ ስም ምርጫዉ ፍትሃዊ እና ዴሞክራስያዊ ነዉ ተብሎ የተሰጠዉ መግለጫ አይወክለንምም ብለዋል።
ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ