1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአዲስ አበባ ከተማ የቦምብ ጥቃት ሁለት ሰዎች ተገደሉ

እሑድ፣ ሚያዝያ 10 2013

በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ የቦንብ ፍንዳታ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአዲስ ፖሊስ ኮሚሽን በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጹ አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/3sCLq
Logo der Polizei-Kommission Addis Abebas
ምስል Addis Ababa Police Commission

በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ የቦንብ ፍንዳታ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአዲስ ፖሊስ ኮሚሽን በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጹ አስታወቀ። ፖሊስ እንዳለው የቦምብ ፍንዳታው ዛሬ እሁድ ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ሚትሮሎጂ ፊት ለፊት ለልማት በተዘጋጀ ቦታ ላይ ነው የተከሰተው ። በአደጋው የሁለት ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ አንድ ግለሰብ በፅኑ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን በክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መርማሪ የሆኑት ረዳት ኢንስፔክተር ዳንኤል ታፈሰ ገልፀዋል፡፡ የፍንዳታውን ምክንያት እና ፈጻሚዎችን ለማወቅ ፖሊስ በምርመራ ሂደት ላይ ይገኛል ብለዋል። ነገር ግን በፍንዳታው ወቅት ዕድሜያቸው ከ50 እስከ 55 የሚገመቱ አንድ ወንድ እና ሁለት ሴቶች በአካባቢው የነበሩ ሰዎችን እየገፈታተሩ ወደ ስፍራው መግባታቸው መታወቁን ፖሊስ ጠቅሷል። በተጨማሪም በፍንዳታው ሕይወቱ ካለፈ ግለሰብ ኪስ ውስጥ ሌላ ያልፈነዳ ቦምብ መገኘቱን ፖሊስ ገልጿል።

ታምራት ዲንሳ

ልደት አበበ