1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአዲስ አበባ እና ዙሪያው በዘጠኝ ወራት የደረሱ አደጋዎች

ሰኞ፣ ሚያዝያ 10 2014

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ እና አቅራቢያው በሚገኙ አከባቢዎች ከ370 በላይ አደጋዎች መከሰታቸውን የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳት እና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/4A4dq
Äthiopien Addis Abeba | Solomon Fisseha, Commissioner of Addis Ababa City Fire and Emergency
ምስል Seyoum Getu/DW

የደረሱ አደጋዎች መግለጫ

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ እና አቅራቢያው በሚገኙ አከባቢዎች ከ370 በላይ አደጋዎች መከሰታቸውን የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳት እና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ሰሎሞን ፍሰሐ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ እንዳረጋገጡት፤ በእነዚህ ዘጠኝ ወራት ከተከሰቱ 377 የተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ አደጋዎች 251 ያህሉ የእሳት አደጋ ክስተት ነበር። 

በአደጋዎቹ በነዚህ ወራት 104 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በተጨማሪነት ሊደርስ የነበረውን የ55 ሰዎች ሕይወት ከአደጋ ማትረፍ መቻሉም ነው የተገለፀው። ውድመት ባስከተሉት አደጋዎቹ ንብረት ላይ የደረሰውን አኃዛዊ ግምት ግን ኮሚሽኑ ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል፡፡

ስዩም ጌቱ

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ