በአውሮጳ የኮሮና ክትባት መጓተት
ሐሙስ፣ የካቲት 4 2013ማስታወቂያ
በአውሮጳ የኮሮና ክትባት ሂደት መጓተትና በሩሲያ አንጻር በሚወሰዱ አቋሞች ላይ የፓርላማ አባላትና አንዳንድ አባል መንግሥታት ጭምር በኮሚሽኑ ባለሥልጣናት ላይ ተቃውሞ እያቀረቡ ነው። የአውሮጳ ሕብረት ኮሚሽን የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ከትናንት በስተያ በአውሮጳ ፓርላማ ቀርበው ባለፈው ዓርብ በሩሲያ ካደረጉት ጉብኝት ጋር ተያይዞና በሩሲያ ላይም ሕብረቱ ባለው ፖሊሲ በሚቀርብባቸው ወቀሳዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የኮሚሽኑ ፕሬዝደንት ዑርዙላ ፎንደር ላይንም በፓርላማው ቀርበው የኮሚሽኑን የኮሮና ክትባት ስልት በማብራራት ከሚቀርብባቸው ክሶችና ወቀሳዎች ራሳቸውንና ኮሚሽናቸውን ተከላክለዋል።
ገበያው ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ