አስተያየት በአውሮጳ ኅብረት ውሳኔዎች ላይ
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 27 2013ማስታወቂያ
የአውሮጳ ሕብረት ስድስተኛውን የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ እንደማይታዘብ ማሳወቁ ሕብረቱ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ላይ ያሳያቸውን አሉታዊ ተፅዕኖዎች እንደሚያመለክት በውሳኔው ላይ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ ተናገሩ።ሕብረቱ በምርጫ ታዛቢነት ቢሳተፍ ለምርጫው ተዓማኒነት ትልቅ እድል እንደነበር የገለፁት አስተያየት ሰጪዎቹ ይህ አለመሆኑ ሕብረቱ ይበልጥ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን ለማሳደር እድል እንደሚፈጥርለት ገልጸዋል። በዚህ የተነሳም ኢትዮጵያ ዘላቂ ጥቅሟን ለማስጠበቅ አሁንም ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ሥራዎችን ልታከናውን ይገባል ብለዋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ