1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአንበጣ መንጋ ሰብላቸው የወደመባቸው አርሶ አደሮች በችግር ላይ መውደቃቸውን ገለጹ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 4 2012

በደቡብ ክልል በተከሰተ የአንበጣ መንጋ ሰብላቸው የወደመባቸው አርሶ አደሮች በችግር ላይ መውደቃቸውን እየገለጹ ይገኛሉ ።አርሶአደሮቹ እንዳሉት መንጋው ከባለፈው ዓመት መግቢያ አንስቶ በአርሻ ማሳቸው ላይ ባደረሰው ጉዳት ከነቤተሰቦቻቸው ለምግብ አጥረት ተዳርገዋል ፣ ለዘር የሚሆን አህልም በአጃቸው ላይ የለም ።

https://p.dw.com/p/3c7iU
Global Ideas Kenia Heuschreckenplage
ምስል picture-alliance/AP Photo/B. Curtis

በደቡብ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች አንበጣ የምግብ ዋስትና ላይ ስጋት ደቅኗል።

በደቡብ ክልል በተከሰተ የአንበጣ መንጋ ሰብላቸው የወደመባቸው አርሶ አደሮች በችግር ላይ መውደቃቸውን እየገለጹ ይገኛሉ ።አርሶአደሮቹ እንዳሉት መንጋው ከባለፈው ዓመት መግቢያ አንስቶ በአርሻ ማሳቸው ላይ ባደረሰው ጉዳት ከነቤተሰቦቻቸው ለምግብ አጥረት ተዳርገዋል ፣ ለዘር የሚሆን አህልም በአጃቸው ላይ የለም ።በአንበጣ መንጋ ሰብላቸው የወደመባቸው አርሶአደሮችን የመለየት ስራ መከናወኑን የገለጹት የክልሉ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ የስራ ሃላፊዎች በበኩላቸው በልየታው መሰረት ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ የቅደም ዝግጅት ስራ በመደረግ ላይ ይገኛል ብለዋል ።

ሸዋንግዛው ወጋየሁ 

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ