1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ መልእክተኛ ጉብኝት የመንግሥት አስተያየት

ሰኞ፣ ነሐሴ 10 2013

ወደ ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ የሚሄዱት በአሜሪካን የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ከኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በተጨማሪ በዘጠኝ ቀናት ጉብኝታቸው ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችም ጎራ ይላሉ።

https://p.dw.com/p/3z3OF
USA Jeffrey Feltman in New York
ምስል picture-alliance/Pacific Press/A. Lohr-Jones

የአምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ጉብኝት

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን፤ ለሦስተኛ ዙር የአፍሪካ ቀንድ ጉብኝት ጅቡቲ ገብተዋል። ወደ ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ የሚሄዱት አምባሳደር ፌልትማን ከኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በተጨማሪ በዘጠኝ ቀናት ጉብኝታቸው ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችም ጎራ ይላሉ። በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ለዘጠኝ ወራት የዘለቀው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እልባት በሚያገኝበት ሁኔታ ላይ መምከር ዐቢይ ትኩረታቸው የሆነው መልእክተኛው በኢትዮጵያ ተቀናቃኝ ኃይሎች «ወደ ድርድር ጠረጴዛ በአስቸኳይ እንዲመጡ» ነው ጥሪያቸው። በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ግን ይህን ጥሪ መቀበል ቀላል የሆነ አይመስልም። የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣን እና በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ በተለይም ለዶይቼ ቬለ ጥያቄውን መቀበል አስቸጋሪ ነው ብለዋል። 

ስዩም ጌቱ 

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ