1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማሮ ልዩ ወረዳ ታጣቂዎች 6 ሰዉ ገደሉ

ማክሰኞ፣ የካቲት 30 2013

በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ስድስት ሰዎች ተገደሉ። ሰዎቹ የተገደሉት ልዩ ወረዳውን ከኦሮሚያ ምዕራብ ጉጂ ዞን በሚዋስነውና ዳኖ በተባለ የገጠር ቀበሌ ውስጥ ነው። በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል የልዩ ወረዳው የብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊና አንድ የፖሊስ ባልደረባ እንደሚገኙበት ተገልጧል።

https://p.dw.com/p/3qP4B
Karte Sodo Ethiopia ENG

በጥቃቱ 6 ሰዎች መገደላቸው ተገልጧል

በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ስድስት ሰዎች ተገደሉ። ሰዎቹ የተገደሉት ልዩ ወረዳውን ከኦሮሚያ ምዕራብ ጉጂ ዞን በሚዋስነውና ዳኖ በተባለ የገጠር ቀበሌ ውስጥ ነው። በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል የልዩ ወረዳው የብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊና አንድ የፖሊስ ባልደረባ እንደሚገኙበት የአማሮ ልዩ ወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ባለስልጣናት ገልጸዋል። ጥቃቱ የደረሰው የአማሮ እና የጉጂ ተጎራባች ነዋሪዎች በእርቅ ጉዳይ ላይ ለመምከር ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሁለቱ መስተዳደር አመራር ጋር በተሰበሰቡበት ወቅት ነው።  ባለፉት ሦስት ዓመታት በደረሱ ተመሳሳይ  ጥቃቶች ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች መገደላቸውን ጥናቶች ያመለክታሉ። በሺህዎ የሚቆጠሩም ከቀዬያቸው ተፈናቅለዋል። 

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ