1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል የሚፈጸሙ ጥቃቶችና በምርጫ ላይ የሚያሳድሩት ተጽእኖ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 18 2013

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መ/ር አቶ ቻላቸው ታረቀኝ የአማራ ክልልን ሰላም ለመንሳት በተለያዩ አቅጣጫዎች ትንኮሳዎች እየተደረጉ ነው ብለዋል።የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህም የክልሉን ሰላም ለማናጋት የታጠቁ ኃይሎች በሁሉም አቅጣጫ ጥቃት ለመፈፀም እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3sb2o
Äthiopien Bahir Dar | Proteste gegen Ermordung und Vertreibung von ethnischen Amharas
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

በአማራ ክልል የሚፈጸሙ ጥቃቶችና በምርጫ ላይ የሚያሳድሩት ተጽእኖ

 

በአማራ ክልል የሚፈጸሙ ጥቃቶችና ያን ተከትሎ የሚታዩ ተቃውሞዎች በክልሉ በሚደረገው ምርጫ ላይ ተፅዕኖ ሊያደርሱ እንደሚችሉ አንድ የፖለቲካ ምሁር ተናገሩ።ዶቼቬለ ያነጋገራቸው እኚሁ የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ምሁር እንዳሳሰቡት የአማራ ክልል መንግስት የፀጥታ ኃይሉን አጠናክሮ የክልሉን ሰላም ማስጠበቅ አለበት።ያም ሆኖ ህብረተሰቡም መብቱን በመጠቀም ወኪሎችን መምረጥ እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፐለቲካ ሳይንስ መምህር አቶ ቻላቸው ታረቀኝ ዛሬ ለዶይቼ ቬለ እንደገለፁት የአማራ ክልልን ሰላም ለመንሳት በተለያዩ አቅጣጫዎች ትንኮሳዎች እየተደረጉ ነው።የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህም ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ የክልሉን ሰላም ለማናጋት የታጠቁ ኃይሎች በሁሉም አቅጣጫ ጥቃት ለመፈፀም እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ አመልክተዋል።የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲው ምሁር አቶ ቻላቸው “በክልሉ ያንዣበበውን የሰላም ስጋት ለማስወገድ የአማራ ክልል መንግስት ሁሉንም የፀጥታ አካላት በማቀናጀት ህብረተሰቡን ከተደቀነበት ስጋት ሊያወጣው ይገባል” ብለዋል፡፡በአማራ ክልል ያለው አሁናዊ ሁኔታ በቀጣዩ አገራዊ ምርጫ በተለይ በአማራ ክልል ጥላ ሊያጠላበት እንደሚችል አቶ ቻላቸው ተናግረዋል።አለመምረጥ ሌላ ችግር ሊያመጣ ይችላል ያሉት አቶ ቻላቸው፣ ህብረተሰቡ ካርዱን አውጥቶ መብቱን እንዲጠቀምም መክረዋል።እስካሁን በአማራ ክልል ምን ያህል መራጮች እንደተመዘገቡ ለማወቅ የክልሉን ምርጫ ቦርድ ኃላፊ አቶ መኳንንት መከተን ጠይቀን “ከአንዳንድ ሁኔታዎች ጋር ተያይዞ የጠራ መረጃ የለንም” ብለዋል።በአማራ ክልል 18 የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫው ይሳተፋሉ።

አለምነው መኮንን

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ