1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወባ ወረርሽኝ ሌላ የጤና ስጋት

ማክሰኞ፣ ግንቦት 18 2012

በአማራ ክልል 25 ወረዳዎች የወባ ወረርሽኝ መከሰቱን የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አስታወቀ፤ እስካሁን ከ400 ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው መጠቃታቸውን ኢንስቲቲዩቱ ገልጿል። ቁጥሩ ባለፉት ዓመታት ከተመዘገቡት ሁሉ የላቀ ነው ሲል ሌላ የጤና ስጋት መደቀኑን አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/3cjhQ
Äthiopien Ausbruch der Malaria-Epidemie in der Region Amhara
ምስል DW/Alemnew Mekennon

በአማራ ክልል የወባ ወረርሽኝ ተከስቷል

በአማራ ክልል 25 ወረዳዎች የወባ ወረርሽኝ መከሰቱን የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አስታወቀ፤ እስካሁን ከ400 ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው መጠቃታቸውን ኢንስቲቲዩቱ ገልጿል። ቁጥሩ ባለፉት ዓመታት ከተመዘገቡት ሁሉ የላቀ ነው ሲል ሌላ የጤና ስጋት መደቀኑን አስታውቋል።የኮሮና ወረርሽኝ እጅግ እየከፋ በሄደበት ባሁኑ ወቅት ሌሎች በሽታዎችም እየተስፋፉ ለህብረተሰቡ የእለት ከእለት እንቅስቃሴ ፈተና እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ከጤና ባለሙያው እስከ አመራሩ ትኩረቱን ወደ ኮሮና መከላከል ባደረገበት ባሁኑ ጊዜ ወባ ሌላ ስጋት ሆኖ ብቅ ብሏል፡፡የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ተቋም የወባ ክፍል ባለሙያ አቶ አማረ ደስታ ሰሞኑን እንደገለፁት በክልሉ በሚገኙ 25 ወረዳዎች ወባ በወረርሽኝ መልክ ተከስቷል፡፡አቶ አማረ የዚህ ዓመት የወባ ታማሚዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ሲነፃፀር እጥፍ በሚባል ደረጃ ጨምሯል፡፡በአማራ ክልል የደቡብ ጎንደር ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙላት አሻግሬ በበኩላቸው በደቡብ ጎንደር ዞን በበሽታው 2 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን 1900 ሰዎች ደግሞ በበሽታው መጠቃታቸውን አብራርተዋል፡፡ህብረተሰቡ አጎበር ባግባቡ በመጠቀምና ውሀ ያቆሩ ቦታዎችን በማፋሰስ ራሱንና ቤተሰቡን ከበሽታው እንዲከላከል አቶ ሙላት መክረዋል፡፡በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ የሐሙሲት ጤና ጣቢያ ኃላፊ አቶ መራ እንዳዬ ከፍተኛ ቁጥር ያለው በሽተኛ በጤና ጣቢያቸው መታከሙን በፅኑ የታመሙት ደግሞ ወደ ባሕር ዳር ለከፍተኛ ህክምና መላካቸውን ተናግረዋል፡፡በአማራ ክልል ከሚገኙ 167 ወረዳዎች በሰሜን ሽዋ ዞን ከሚገኘው አንጎለላ ወረዳ በስተቀር 166ቱ የወባ ታማሚ ሪፖርት በየዓመቱ ሪፖርት እንደሚደረግ ለማወቅ ችለናል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሐመድ