1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል የትምርት ጥራት መጓደል 

ሐሙስ፣ ኅዳር 6 2011

በአማራ ክልል በትምህርቱ ዘርፍ የሚታዩ ችግሮች ለትምህርት ጥራት ማሽቆልቆል አይነተኛ ምክንያት መሆናቸውን ወላጆች፣ መምህራንና ተማሪዎች አመለከቱ፡፡ እንደ አስተያየት ሰጪዎች አራተኛ ክፍል ደርሰው ስማቸውን ማጻፍ የማይችሉ ተማሪዎች ቁጥር ቀላል አየደለም።

https://p.dw.com/p/38LJq
Global Media Forum KLICK! 2012 Horst Frommont 3
ምስል Horst Frommont

በአማራ ክልል በትምህርቱ ዘርፍ የሚታዩ ችግሮች ለትምህርት ጥራት ማሽቆልቆል አይነተኛ ምክንያት መሆናቸውን ወላጆች፣ መምህራንና ተማሪዎች አመለከቱ፡፡ እንደ አስተያየት ሰጪዎች አራተኛ ክፍል ደርሰው ስማቸውን ማጻፍ የማይችሉ ተማሪዎች ቁጥር ቀላል አይደለም። የመምህራንና  የመፀሐፍትእጥረት፣የመምህራንና የወላጆች ጥምረት መላላት የቁጥጥርና ክትትል አለመኖር፣ የቤተሙከራ ኬሚካሎች እጥረት፣ የመምሕራን የጊዜ አጠቃቀም ችግርና ሌሎችም ተግዳሮቶች ለትምህርት ጥራት መጓደል ዋና ዋና ምክንቶች  ናቸው፡፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በበኩሉ የተጠቀሱ ችግሮች አብዛኛዎቹ ትክክል መሆናቸውን ያምናል፤ የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ይልቃል ከፍአለ እንደሚሉት ችግሮችን ለማስወገድና የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል፡፡

 

አለምነዉ መኮንን 


አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ