1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል ሕወሓት በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች 200,000 ሰዎች ተፈናቅለዋል

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 27 2013

ህወሓት በፈጠረው ቀውስ የኢትዮጵያ መንግስት የተናጠል ተኩስ ካደረገ ወዲህ 150ሺህ ወገኖች ከራያ ቆቦና ሌሎች 50ሺህ የሚሆኑት ደግሞ በሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው በችግር ላይ እንደሚገኙ አቶ ግዛቸው ገልፀዋል፡፡ እንደዚያም ሆኖ ረጂ ድርጅቶችና ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ የእርዳታ እጁን ለመዘርጋት አልፈለገም ብለዋል።

https://p.dw.com/p/3yTMC
Äthiopien Gizachew Muluneh General Director Amhara Communication Office Bahar Dar
ምስል Alemenew Mekonnen/DW

በአማራ ክልል ከ200,000 ሰዎች ባለይ የሰብአዊ ድጋፍ ይሻሉ

የኢትዮጵያ መንግስት የተናጠል ተኩስ ካደረገ ወዲህ ህወሓት በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች 200ሺህ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀሉን የአማራ ክልል መንግስት አስታወቀ፣ ረጂ ድርጅቶች ተፈናቃዮችን ለማገዝ ምንም ተነሳሽነት አላሳዩም ሲል የክለሉ መንግስት ተችቷል፣ የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ቢሮ የዓለም የምግብ ፕሮግራም በቅርቡ እገዛ እንደሚያደርግ አመልክቷል፡፡

የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዘቻው ሙሉነህ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት መግለጫ “አሸባሪ” ያሉት ህወሓት በኃይል በወረራቸው የሰሜን አማራ አካባቢዎች ግድያ ድብደባ፣ ዝርፊያና ሌሎችንም ተግባራት ይፈፅማል ብለዋል፡፡

ህወሓት በፈጠረው ቀውስ የኢትዮጵያ መንግስት የተናጠል ተኩስ ካደረገ ወዲህ 150ሺህ ወገኖች ከራያ ቆቦና ሌሎች 50ሺህ የሚሆኑት ደግሞ በሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው በችግር ላይ እንደሚገኙም ገልፀዋል፡፡ ያም ሆኖ ረጂ ድርጅቶችና ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ የእርዳታ እጁን ለመዘርጋት አልፈለገም ያሉት አቶ ግዛቸው፣ ይህም ግልፅየሆነ አድልዎ ነው ሲሉ ረጂ ድርጅቶችንና ዓለምአቀፉን ማህበረሰብ ነቅፈዋል፡፡

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን የቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ዳሬክተር አቶ ጀንበሩ ደሴ ተጠይቀው “ለተረጂዎቹ አስፈላጊው እገዛ እንዲደረግ የዓለም አቀፉ የምግብ ፕሮግራም (WFP) ፈቃድ ተሰጥቶታል” ብለዋል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (United Nations Office for Coordination of Humanitarian Affairs - UNOCHA) አንድ ባለሙያ ጉዳዩን ከአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ማግኘት እንደምችል ጠቁመው እነርሱም ከዛ የተለየ ነገር እንደማያውቁና ዝርዝር ጉዳዩን ለመግለፅ አልፈለጉም፡፡ በአጠቃላይ በአማራ ክልል በሌሎች ምክንያቶች ጭምር ከ400ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙም የክልሉ መንግስት በመግለጫው አመልክቷል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሐመድ