በነበቀለ ገርባ መዝገብና በሌሎች የፍርድ ቤት ዉሎ
ሰኞ፣ ሐምሌ 6 2012ማስታወቂያ
የፌደራል የመጀመርያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በነበቀለ ገርባ መዝገብና በሌሎች በአቃቤ ሕግና በፖሊስ በተያዙ ተጠርጣሪዎች ላይ ፖሊስ የጠየቀዉን የምርመራ ጊዜ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። ዛሬ በ 17 ተጠርጣሪዎች ላይ ፖሊስ ባቀረበዉ የክስ መዝገብ በተጠርጣሪዎች ላይ ከተያዙት ክሶች መካከል ብሔር ብሔረሰቦችን እንዲጋጩ በማድረግ ፤ የኦሮምያ ባለስልጣናትን የመግደል ሙከራ ፤ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን አስክሬን እንዲጉላላ በማድረግ የተሰኙት ክሶች ከብዙ ጥቂቶች መሆናቸዉ ተመልክቶአል። ከአቶ በቀለ ገርባ ጋር ዛሬ ፍርድቤት ከቀረቡት ውሰጥ ከ10 የአቶ ጀዋር መሐመድ አጃቢዎች ዘጠኙና የአቶ በቀለ ገርባ ሁለት ልጆች ይገኙበታል ። የወንጀሉ አፈፃፀም ዉስብስብነት በመግለፅ ፖሊስ ተጨማሪ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠዉ ቢጠይቅም ፖሊስ የጠየቀዉ የ 14 ቀናት ጊዜ ሊፈቀድለት አይገባም በሚል ጠበቆች በመከራከራቸዉ ፍርድ ቤቱ ዉሳኔ ለመስጠት ለሐምሌ 9 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱ ታዉቋል።
ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር
ታምራት ዲንሳ
ነጋሽ መሐመድ