1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኃይል መቋረጥ ሀይደር ሆስፒታል ሥራ አቆመ

ሐሙስ፣ ግንቦት 25 2014

በትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ሆስፒታሎችን ጨምሮ ሌሎች ኃይል የሚሹ ተቋማት ከሥራ ውጭ መሆናቸው ተገለፀ። እየተቆራረጠም ቢሆን በክልሉ መንግስት ይቀርብ የነበረ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰሞኑን ሙሉ በሙሉ መቋረጡ ተዘግቧል።

https://p.dw.com/p/4CC4N
Äthiopien | Haider Hospital in Mekelle
ምስል Million Hailessilasie/DW

የኃይል አቅርቦት ሙሉ በሙሉ መቋረጡ ተገልጧል

በትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ሆስፒታሎችን ጨምሮ ሌሎች ኃይል የሚሹ ተቋማት ከሥራ ውጭ መሆናቸው ተገለፀ። እየተቆራረጠም ቢሆን በክልሉ መንግስት ይቀርብ የነበረ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰሞኑን ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ፥ በትግራይ ክልል ትልቁ የሕክምና ማእከል ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ጨምሮ በርካታ ተቋማት ሥራ ያቆሙ ሲሆን የህዝቡ ኑሮም በከፍተኛ ደረጃ መጎዳቱን የመቀሌው ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለሥላሴ ዘግቧል። 

በኃይል መቋረጡ ምክንያት የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ሥራ አቁመዋል። የከተማ ነዋሪዎች ለኑሮ የሚያስፈልጋቸውን የሀይል ፍጆታ አጥተው በውድ ዋጋ ወደሚሸጥ እንጨት እና ከሰል ተመልሰዋል፣ የክልሉ ሚድያዎች ሳይቀሩ የስርጭት ሰዓታቸው የተገደበ ሆነዋል።

ትግራይ ክልል ከኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ስርጭት መስመር ውጭ ከሆነች ከ11 ወራት በላይ አልፏል።
 

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ