1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድሬዳዋ ጎርፍ ሰላባዎች ዝክር

ዓርብ፣ ሐምሌ 30 2013

በድሬደዋ ሐምሌ 28 ቀን 1998 ዓ.ም ሌቱን የጣለ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የበርካታ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሀብት ንብረት ወድሟል።ድሬደዋዎች ይህንን ዕለት 500 ሺህ ችግኞችን በአንድ ቀን በመትከል ዘክረውታል፡፡ በችግኝ ተከላው ነዋሪዎች የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሀገር ሽማግሌዎች በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3ye2Q
Äthiopien | Gedenken an Flutopfer in Dire Dawa
ምስል Messay Teklu

ችግኝ ተከላ በድሬደዋ

ከአስራ አምስት አመታት በፊት  ሐምሌ 28 ቀን 1998 ዓ.ም ሌቱን የጣለ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የበርካታ ሰዎችን ህይወት የተነጠቀችው ድሬደዋ  ዕለቱን በአንድ ቀን አምስት መቶ ሺህ ችግኞችን በመትከል አስባለች፡፡ ችግኞችን መትከል እና ተንከባክቦ እንዲፀድቁ ማድረግ ለድሬደዋ የህልውና ጉዳይ መሆኑን አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል፡፡

በድሬደዋ ሐምሌ 28 ቀን 1998 ዓ.ም ሌቱን የጣለ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የበርካታ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሀብት ንብረት ወድሟል፡፡ እጅጉን አሳዛኝ ትውስታን ትቶ ያለፈው ያ ክስተት አስራ አምስት ዓመት ሞላው፡፡ድሬደዋዎች ይህንን ዕለት አምስት መቶ ሺህ ችግኞችን በአንድ ቀን በመትከል ዘክረውታል፡፡ ነዋሪዎች ፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ብቸናዋ ሴት አሰልጣኝ የነበረችው ኢንስትራክተር መሰረት ማኔ እና ከብሔራዊ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች መካከል ወጣት ሰምበቶ አቡ ስለችግኝ ተከላው ለዶቼቬለ አስረድተዋል።

Äthiopien | Gedenken an Flutopfer in Dire Dawa
ምስል Messay Teklu

በድሬደዋ በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሪፈራል ሆስፒታል ችግኝ ተከላ ላይ ያነጋገርናቸው ሻለቃ ራህመቶ ሂርጶ በበኩላቸው ሀገር የምትፈርሰው በጦርነት ብቻ ሳይሆን በሰው ሰራሽ አደጋዎች መሆኑን ጠቅሰው እሱን ለመከላከል ሰራዊቱ የበኩሉን ይወጣል ብለዋል፡፡

ባለፈው አመት በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በአስተዳደሩ ከተማና ገጠር ከተተከሉ ችግኞች 68% (ስልሳ ስምንት በመቶ) የሚሆኑት መፅደቃቸውን የአስተዳደሩ ግብርና ውሀ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ተናግረዋል፡፡

Äthiopien | Gedenken an Flutopfer in Dire Dawa
ምስል Messay Teklu

በከተማና በገጠር አምስት መቶ ሺህ ችግኝ የመትክል መርህ ግብርን ያስጀመሩት የድሬደዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ  ለድሬደዋ የተለየ ጥቅም አለው ባሉት የችግኝ ተከላ ላይ የተገኘው ህብረተሰብ ችግኞችን መንከባከብ አለበት ብለዋል፡፡

በያዝነው ክረምት ሁለት ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ጥረት በሚደረግባት ድሬደዋ በአንድ ቀን ከተተከለው አምስት መቶ ሺህ የዛፍ ችግኝ 70 በመቶው የደን ፣ 26 በመቶ የምርምር ደን እንዲሁም ቀሪው 4 በመቶ የውበት ዛፍ ያካተተ መሆኑ ተገልጧል፡፡

መሳይ መኮንን

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ