1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራይ የፊስቱላ ተጠቂዎች ቁጥር አድጓል

ዓርብ፣ ግንቦት 16 2016

የትግራይ ጤና ቢሮ እንደሚለው፣ከጦርነቱ በፊት በክልሉ ከአንድ ሺህ ሴቶች ለፌስቱላ የሚዳርጉ ሶስት ነበሩ አሁን ከአንድ ሺሁ 26ቱ ለፊስቱላ ይዳረጋሉ። በጦርነቱ ጾታዊ ጥቃት መባባሱ የሕክምና ተቋማት መውደም እና አገልግሎት አለመስጠት በአጠቃላይ የጤና ስርዓቱ መፍረስ ፌስቱላ በትግራይ እንዲያሻቅብ እንዳደረገው የሕክምና ባለሙያዎች ይገልፃሉ።

https://p.dw.com/p/4gFsz
Äthiopien | Tigray - Patient
ምስል Million Hailesilassie/DW

በትግራይ የፊስቱላ ተጠቂዎች ቁጥር አድጓል

በጦርነት፣ በጤና ተቋማት አገልግሎት ውሱንነት እና በሌሎች ችግሮች ሰበብ በትግራይ በፌስቱላ የሚጠቁ ሴቶች ቁጥር በከፍተኛ መጠን ማደጉ ተገለፀ። እንደ የትግራይ ጤና ቢሮ መረጃ ከጦርነቱ በፊት በትግራይ ከአንድ ሺህ ሴቶች ለፌስቱላ የሚዳርጉ ሶስት እንደነበረ የሚጠቅስ ሲሆን አሁን ግን፥ በትግራይ ከአንድ ሺህ ሴቶች ለፌስቱላ  የሚዳርጉት ቁጥር ወደ 26 ማደጉ ተነግሯል።

በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ የጤና ስርዓቱ በመፍረሱ ፌስቱላን ጨምሮ የተለያዩ በሽታዎች ስርጭት መስፋቱ ይነገራል።እንደ የትግራይ ጤና ቢሮ አሀዛዊ መረጃ ከጦርነቱ በፊት በትግራይ ከአንድ ሺህ ሴቶች መካከልለፌስቱላ የሚዳርጉ ሶስት እንደነበረ የሚያወሳ ሲሆን አሁን ላይ ባለው ግን፥ ከአንድ ሺህ ሴቶች በትግራይ በፌስቱላ የሚጠቁት ቁጥር ወደ 26 ማደጉ ይገልፃል። በጦርነቱና ከጦርነቱ በኋላ የተፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶች፣ የሕክምና ተቋማት መውደም እና አገልግሎት አለመስጠት በአጠቃላይ የጤና ስርዓቱ መፍረስ ፌስቱላ በትግራይ ለመጥፋት ከመቃረብ ይልቅ  በከፍተኛ ደረጃ ወደ ማሻቀብ እንደመራው የሕክምና ባለሙያዎች እና አጥኚዎች ይገልፃሉ። በመቐለ የሚገኘው ሃምሊን ካትሪን ፌስቱላ ሕክምና ማእከል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር መልአኩ አብርሃ በትግራይ በፌስቱላ የሚጠቁ ቁጥር በከፍተኛ መጠን ማደጉ ይናገራሉ።

ሀሚሊን ፊስቱላ በመቀሌ የፊስቱላ ህክምና የሚሰጥ ማዕከል
ሀሚሊን ፊስቱላ በመቀሌ የፊስቱላ ህክምና የሚሰጥ ማዕከልምስል Million Hailesilassie/DW

በስፋት ሴቶች ላይ የሚታየው ይህ የጤና ችግር አሳሳቢ መሆኑ የሚያነሱት ደግሞ የመቐለ ሴቶች ማሕበር ስራአስኪያጅ ወይዘሮ ርግበ አብርሃ ናቸው። የፊስቱላ መታሰቢያ ዕለት በኢትዮጵያ፣የትግራይ ጤና ቢሮ እንደሚለው ለፌስቱላ ጨምሮ ለተለያዩ የጤና ችግሮች ምክንያት የሚሆነው ከጤና ጣብያ ውጭ የሚደረግ ወሊድ መጨመሩ የሚገልፅ ሲሆን ይህ ተከትሎ የእናቶች ሞት መጠንም ከ22 ዓመት በፊት ወደ ነበረበት መመለሱ ይገልፃል። የትግራይ ጤና ቢሮ ባለሙያው ዶክተር ስምኦን ገብረፃዲቅ የፌስቱላ በሽታ ለመቀነስ የጤና ተቋማት አገልግሎት ማጠናከር ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ይናገራሉ።

የተባበሩት መንግስት ድርጅት ግንቦት 23 ወይም ግንቦት 15 ዓለምአቀፍ ፌስቱላ የመከላከል ቀን ብሎ ሰይሞ በዕለቱ ግንዛቤ የሚፈጥሩ መልእክቶች ያስተላልፋል። ይህንኑ በማስመልከት ትላንት በመቐለ ፌስቱላ መከላከል የተሰኘ የጤና ባለሙያዎች፣ የሴቶች ማሕበራት ተወካዮች፣ ተጎጂዎች እና ሌሎች ያሳተፈ የግንዛቤ ማሳደግ መድረግ ተካሂዷል።

 

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ