1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፌስቱላን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ዘመቻ ሊደረግ ነው

ማክሰኞ፣ ጥር 16 2015

ስልሳ ዓመታት የሆነዉ ሐምሊን ፌስቱላ ኢትዮጵያ ከስላሺ በላይ እናቶችን እና እህቶችን ህክምናን እና የሥነ-ልቦና ድጋፍ ሰጥቷል፤ የአቅም ግንባታም አድርጓል። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በኢትዮጵያ ለፌስቱላ በሽታ የሚከሰተው ከሦስት ቀናት በላይ ምጥ የቆየባቸው እናቶች ላይ እንዲሁም በቀዶ ሕክምናና ከካንሰር በሽታ ጋር በተያያዘ ነው።

https://p.dw.com/p/4MeID
Krankensaal im Fistula Krankenhaus in Abbis Abeba
ምስል Fistula e.V.

በገጠራማው የአገራችን ክፍል የሚኖሩ እናቶችና እህቶች ፊስቱላ በህክምና ሊድን እንደሚችል አያዉቁም

የፌስቱላ በሽታ አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በሌሎች የኢትዮጵያ ክልል ከተሞች በአሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ፣ የጤና ሚኒስቴርና ሐምሊን ፌስቱላ በያዝነው ወር መጀመሪያ ላይ አስታውቀዋል።  ፌስቱላ ሊታከም እና ሊድን የሚችል በሽታ ቢሆንም  ማህበረሰቡ መረጃውን በአግባቡ የማግኘት ችግር እንዳለ ይታያል።  ታዲያ ይህንን ክፍተት ለማጥበብ በቀጣይ ቀናት  ከወረዳ እስከ ወረዳ የተባለ ፕሮጀክት ሐምሊን ፌስቱላ ሊተገበር  መሆኑን አቶ ተስፋዬ ማሞ የሐምሊን ፌስቱላ ኢትዮጵያ ከዋና ስራ አስፈጻሚ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል ።«የኛ መስራች ዶክተር ካትሪን ሐምሊን በአንድ ወቅት ፌስቱላ በእኔ እድኔ አይጠፋም በእናንተ እድሜ ግን ሊጠፈ ይችላል ባሉት መሰረት  ትልቅ ፕሮግራም አዘጋጅተን በቀጣይ ወር ተግባራዊ ልናደርገው ነው ይህ ፕሮግራም ከወረዳ እስከ ወረዳ ይባላል ምን ማለት ነው ፌስቱላን ከየወረዳው የማጥፋት ዘመቻ ልንጀምር ነው። ስለዚህ በእያንዳንዱ ወረዳ በየ መንደሮች እየሄድን የፌስቱላ ችግር ያለባቸውን እየለየን ወደ እኛ የህክምና ጣቢያዎች ለማምጣት እና ህክምና ለመስጠት ፕሮግራም ቀርፀን አሁን በቀጣይ ቀናት ሙከራ ልንጀምር ተዘጋጅተናል» 

ከወረዳ  እስከ ወረዳ ሙከራ  በቀጣይ 10 ቀናት ውስጥ በኢሊባቡር  እንደሚጀመር የተናገሩት  አቶ ተስፋዬ ከዚህ ወረዳ የሚወሰድ ተሞክሮ በቀጣይ ወራት ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው ።

የዚህ ዘመቻ አስፈላጊነት ከእዚህ በፊት የፌስቱላ ታማሚዎችን ለማግኘት የሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ባደረገው ዘመቻ ከ30 እና 40 ዓመት በላይ በዚህ ችግር የቆዩ እናቶች እድሜያቸው 65 እና ከዚያ በላይ የሆኑ በተለያዩ ገጠራማ ስፍራዎች በመገኘታቸው ነው። 

Alternative Nobelpreise für Klimaschützer
ዶ/ር ሐምሊን ከፌስቱላ ታካሚ ኢትዮጵያዉያን ጋርምስል DPA

«በርካታ በችግሩ ውስጥ ያሉ እናቶች እና እህቶች ከችግራቸው ይላቀቃሉ ቢሆንም አሁንም በገጠራማው የአገራችን ክፍል የሚኖሩ እናቶች እና እህቶች ፊስቱላ በህክምና ሊድን እንደሚችል በቂ እውቀት የላቸውም» ያሉት አቶ ተስፋዬ በወረዳ እስከ ወረዳ ፕሮግራም ፌስቱላን 100% ማጥፋት ባይችልም ከዚህ በፊት የፊስቱላ ህምም ኖሯቸው ህክምና ያላገኙ ሴቶችን ቁጥር ዜሮ ማድረስ ዋናው እቅዳችን ነው ብለዋል።

ከቀናት በኃላ የሚጀመረው ፌስቱላን ከየወረዳው ማጥፋት እቅድ ‹‹ከወረዳ እስከ ወረዳ›› ፕሮግራም ሙከራ ከተደረገ በኃላ  በአገራችን ውስጥ ባሉ 800 ወረዳዎች ላይ ተደራሽ እንዲሆን ታቅዷል። በሐምሊን ፌስቱላ ኢትዮጵያ በ2014 ዓ.ም ከ2,500 እስከ 3000 የሚደርሱ   እናቶች የፌስቱላ ሕክምና አግኝተዋል።

Äthiopien | Tigray - Hamlin Fistula
ሐምሊን ፌስቱላ ምስል Million Hailesilassie/DW

የስልሳ ዓመታት እድሜ ያስቆጠረው ሐምሊን ፌስቱላ ኢትዮጵያ ከስላሺ በላይ ለሆኑ እናቶች እና እህቶች ህክምና እና የሥነ-ልቦና ድጋፍ እንዲሁም የአቅም ግንባታ አድርጓል። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በኢትዮጵያ ለፌስቱላ በሽታ የሚከሰተው በብዛት የሚከሰተው ከሦስት ቀናት በላይ ምጥ የቆየባቸው እናቶች ላይ እንዲሁም በቀዶ ሕክምናና ከካንሰር በሽታ ጋር በተያያዘ ነው።

ማኅሌት ፋሲል 

ታምራት ዲንሳ