በትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት እንዴት እየሄደ ነው?
ሰኞ፣ ኅዳር 28 2013ማስታወቂያ
በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት የተጎዱ ዜጎች ሰብዓዊ እርዳታ እንዲያገኙ ማድረግ፣ ግጭት ሸሽተው ወደ ጎረቤት ሀገራት የተሰደዱትን መመለስ እና መሰረታዊ ግልጋሎቶችን መልሶ ማስጀመር የቀጣይ ዋናው የመንግሥት ትኩረት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስታውቃል።የተባበሩት መንግሥታት በበኩሉ በክልሉ ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረግ ውጊያ አሁንም መቀጠሉ እንቅፋት እንደሆነበት ጠቅሷል።በሌላ በኩል በትግራይ ክልል የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞች የምግብ አቅርቦት መመናመን እንዳሳሰበውም ድርጅቱ አስታውቃል። በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልላዊ መንግሥት መካከል የተፈጠረው ጦርነት መቀሌ በመከላከያ ሠራዊት እጅ መግባቷን ተከትሎ መጠናቀቁ ቢነገርም አሁንም ውጊያ አለማብቃቱ የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎችን ለማከናወን አዳጋች መሆኑ ይነገራል።
ሰሎሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
አዜብ ታደሰ