1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርትአፍሪቃ

«ሌላ ዮንቨርስቲ ወስደው ያስተምሩን»

ሰኞ፣ ጥቅምት 1 2014

በትግራይ ክልል አራት ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች መንግሥት ወደ ሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲመድባቸው ጠየቁ።  ዛሬ አዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው ትምህርት ሚኒስቴር በመገኘትና በተወካዮቻቸው በኩል ጥያቄአቸውን ያቀረቡት ተማሪዎቹ «የተቋሙ አመራሮች ስልጠና ላይ ናቸው» የሚል መልስ ተሰጥቷቸዋል።

https://p.dw.com/p/41Wur
Äthiopien Studierende Tigray Universität
ምስል Solomon Muchie/DW

ተማሪዎቹ እና የተማሪ ተወካዮች ለዶይቸ ቬለ እንዳሉት ከትግራይ ክልል ሲወጡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርታቸውን እንደሚያስጨርሳቸው ቃል የገባ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ምንም ተጨባጭ ምላሽ አላገኙም። በክልሉ ካሉ ከአራቱም ዩኒቨርሲቲዎች ከ10 000 በላይ ተማሪዎች መኖራቸውን የተናገሩት አንድ ጥያቄ አቅራቢ በተለይ ለመመረቅ ወራቶች ቀርቷቸው የነበሩት ተማሪዎች ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑን ገልፀዋል። ስለሆነም መንግሥት የእነዚህን ተማሪዎች ጭንቀት ተገንዝቦ ወደተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች መድቦ እንዲያስተምራቸው በሥፍራው ተገኝተው የነበሩ ወላጆችም ጠይቀዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ልደት አበበ

ኂሩት መለሰ