1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራይ ክልል ውሳኔ ላይ የተሰጡ አስተያየቶች 

ዓርብ፣ ጥቅምት 7 2012

ውሳኔውን የደገፉ እርምጃው ተገቢ ነው ሲሉ የተቃወሙት ደግሞ የተማሪዎችን መብት የሚጋፋ እና ለፀብም የሚያነሳሳ ሲሉ ተችተውታል። የአማራ ክልልም አጸፋ ከመውሰድ እንዲቆጠብ ያሳሰቡም አሉ።

https://p.dw.com/p/3RXPr
Karte Äthiopien englisch

በትግራይ ክልል ውሳኔ ላይ የተሰጡ አስተያየቶች 

የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምሕርት ቢሮ የአንደኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የግጭት ስጋት አለብኝ ወደሚለው ወደ አማራ ክልል አልክም ማለቱ እያነጋገረ ነው። ውሳኔውን የደገፉ እርምጃው ተገቢ ነው ሲሉ የተቃወሙት ደግሞ የተማሪዎችን መብት የሚጋፋ እና ለፀብም የሚያነሳሳ ሲሉ ተችተውታል። የአማራ ክልልም የአጸፋ እርምጃ ከመውሰድ እንዲቆጠብ ያሳሰቡም አሉ። ዶቼቬለ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ የፌደራል ትምህርት ሚኒስትርና  የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር የሥራ ኃላፊዎች በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡ ቢጠይቅም «እየተወያየንበት ነው» ሲሉ መልሰዋል። የባሕርዳሩ ወኪላችን ዝርዝሩን ልኮልናል።

ዓለምነው መኮንን

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ