1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራዩ ዉግያ የቀይ መስቀል ሰብዓዊ ድጋፍ 

ማክሰኞ፣ ኅዳር 22 2013

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በትግራይ ክልል ልዩ ኃይል እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ሁሉንም የሰብዓዊ ግልጋሎቶች መስጠቱንና ወደፊትም የተጎዱትን ማቋቋም ላይ እንደሚሰራ ገለፀ።

https://p.dw.com/p/3m4RR
Logo Ethiopian Red Cross Society
ምስል Ethiopian Red Cross Society

እስካሁን ከአንድ ሺህ በላይ የተጠፋፉ ቤተሰቦችን ደኅንነትን ለማሳወቅ ተችሎአል

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በትግራይ ክልል ልዩ ኃይል እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ሁሉንም የሰብዓዊ ግልጋሎቶች መስጠቱንና ወደፊትም የተጎዱትን ማቋቋም ላይ እንደሚሰራ ገለፀ። ከዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ጋር በመሆን ከአንድ ሺህ በላይ የተጠፋፉ ቤተሰቦችን ደኅንነት የማሳወቅ ተግባር መከወኑንም አስታውቃል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ደግሞ ሰብዓዊ እርዳታዎች ተደራሽ እንዲሆኑ በትግራይ ክልል የተቋረጡት መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲመለሱ ጠይቋል።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ