1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቴፒ ከተማ የሚገኙት ተፈናቃዮች አቤቱታ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 16 2011

ከዘጠኝ ወራት በፊት ከደቡብ ክልል ሸካ ዞን የኪ ወረዳ በመፈናቀል በቴፒ ከተማ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ገለጹ።

https://p.dw.com/p/3OKkY
Äthiopien Stadt Mizan Teferi
ምስል DW/W. Shewangizaw

«ወደቀያቸው ለመመለስ ስጋት አላቸው»

ተፈናቃዮቹ ወደ ቀድሞ ቀዬቸው ለመመለስ ፍላጎቱ ቢኖራቸውም ቀደም ሲል በመንደሮቹ የግድያ ፣ የዘረፋና የማፈናቀል ድርጊት የፈጸሙ ግለሰቦች እስከአሁን ለሕግ ባለመቅረባቸው ዳግም ተመሳሳይ ጥቃት ሊያደርሱብን ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳላቸው ተናግረዋል።  ዶቼ ቨለ ( DW ) በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው የአካባቢው ባለስልጣናት በበኩላቸው የተፋናቃዮቹን ቅሬታና ስጋት ለመቅረፉ   የሚያስችሉ ሥራዎችን በማከናውን ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። የሀዋሳው ሸዋንግዛው ወጋየሁ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል። 

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ