1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአንዋር መስጊድ አቅራቢያ የተከሰተው ቃጠሎ

ሐሙስ፣ ሰኔ 21 2010

አዲስ አበባ በሚገኘዉ ታላቁ የአንዋር መስጊድ እና በአቅራቢያው ባሉ መደብሮች ላይ ቃጠሎ ደረሰ። ትናንት ከሰባት ሰዓት ከሌሊቱ እስከ ንጋቱ አስራ አንድ ሰዓት በቀጠለው ቃጠሎ የሰው ሕይወት አለመጥፋቱን፣ በመስጊዱ ላይ ንዑስ ጉዳት እንደደረሰ እና ብዙ ንብረት እንደጠፋ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የመሳለሚያ ፖሊስ ባለስልጣን አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/30URY
Die große Anwar-Moschee in Addis Abeba steht in Flammen
ምስል Yared Abegaz

«የቃጠሎው መንስዔ በባለሙያ እየተመረመረ ነው።»

የፖሊስ ባለስልጣን የእሳት አደጋ እና ፖሊስ ባደረጉት ርብርቦሽ እሳቱ ወደ መስጊዱ እንዳይዛመት ለማድረግ መቻላቸውን ቢያስታውቁም፣ በቃጠሎው ንብረት የወደመባቸው አንድ ባለመደብር ግን ከእሳት አደጋ ሰራተኞች በኩል ዝግመት ታይቷል ሲሉ ተናግረዋል።የቃጠሎውን መስዔ ለማወቅ ምርመራ መጀመሩን የፖሊስ ባለስልጣን ገልጸዋል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ