1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በተ.ዐ.ኤሚሬትስ ያሉ የኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞች እጣ ፈንታ

ሐሙስ፣ መስከረም 17 2011

የተባበሩት ዐረብ ኤሚሬትስ መንግሥት በሀገሩ የሚኖሩ፣ግን በሕገ ወጥ መንገድ የሚሰሩ አሁን በሕጋዊነት መኖር ወይም ወደ ሀገራቸው መግባት ለሚፈልጉት የውጭ ዜጎች ከጎርጎሪዮሳዊው ነሃሴ አንድ  እስከ ጥቅምት 30፣ 2018 ዓም፣  ለሶስት ወራት የሚቆይ የምህረት አዋጅ አውጥቷል። የበርካታ ሀገር ዜጎች በዚሁ እድል በመጠቀም ላይ ናቸው።

https://p.dw.com/p/35aMO
UAE Visa-Amnesty für Gastarbeiter in Sicht
ምስል picture-alliance/AP-Photo/K. Jebreili

የምህረት አዋጁ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል የሆኑት ወደ ሀገር መግባት የሚፈልጉ ጥቂት ኢትዮጵያውያን እድሉን በመጠቀም ያለ ምንም ቅጣት ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ግን ከፓስፖርት አቅርቦት ጋር በተያያዘ ችግር የተለያዩ መሰናክሎች እየገጠማቸው መሆኑን ይናገራሉ። ፓስፖርታቸው ያልታደሰ ፤ የጠፋባቸው አዲስ ፓስፖር ማውጣት የጀመሩ ፤ ፓስፖርታቸው በአሰሪዎቻቸውና በኢምሬት ኢምግሬሽን በኢንባሳቸው በኩል የተላከላቸው ዜጎች በአሰራር መጓተትና ወደ ሀገር ቤት የተላከው ፓስፖርት በፍጥነት ስለማይደርስላቸው መቸገራቸውን ስልክ በመደወል ያነጋገርኳቸው ማንነታቸው እንዳይነገር የፈለጉ የዱባይ ነዋሪዎች ገልጸውልኛል ። ኢትዮጵያውያን ዙሪያ ስለሚታየው የፓስፖርት አቅርቦትና በሰነድ አለመሟላት ችግር የአረብ መገናኛ ብዙሃና ትኩረት የሳበ መሆኑ ይጠቀሳል። 

ነቢዩ ሲራክ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ