1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በተለያዩ አካባቢዎች ስላለው የጸጥታ ችግር የኢሰመጉ ማሳሰቢያ

ዓርብ፣ ሐምሌ 16 2013

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ያለው የጸጥታ ችግር ትኩረት እንደሚያሻው አሳሰበ። ኢሰመጉ በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚታየው የጸጥታ ችግር ሰዎች በሕይወት የመኖር፣ የመንቀሳቀስና ንብረት የማፍራት ዋስትና አጥተዋል መባሉንም አመልክቷል።

https://p.dw.com/p/3xwa8
Logo des Ethiopian Human Rights Council
ምስል Ethiopian Human Rights Council

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ማሳሰቢያ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ትናንት ሐምሌ 15/2013 ዓ.ም በማህበራዊ መገናኛ ዜደ  ባሰራጨው መረጃ በአሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጃርዳጋ ጃርተና አሙሩ ወረዳ፣ በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡሌንና ድባጢ ወረዳዎች እንዲሁም  በአማራ ክልልና ትግራይ ክልል ያለውን ጸጥታ ችግር ትኩረት እንደሚሻ ገልጸዋል፡፡ በሆሮ ጉዱ ወለጋ ሁለት ወረዳዎች ውስጥ ብሔርን መሰረት ያደረገ ጥቃቶች መኖራቸውን የገለጸ ሲሆን በዞኑ አሙሩ ወረዳ ወደ 300 የሚጠጉ በሕግ ቁጥጥር ስር የነበሩ ሰዎች ከፖሊስ ጣቢያ መውጣታቸውን እና 30ሺ የሚደርሱ የአማራ ብሔር ተወላጆች ደግሞ ከአካባቢው አትወጡም ተብለው በደህንነት ስጋት ውስጥ እንደሚገኙ አብራርተዋል። በመተከል ዞን ድባጢ እና ቡሌን ወረዳዎችም ከፍተኛ የጸጥታ ችግር መኖሩን መረጃ እንደደረሰውም አመላክቷል። ከአሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽ እና ከዞኑ አስተዳደር በስልክ መረጃ ለማግኘት ያደረኩት ጥረት አልተሳካም። ባለፈው ሳምንት የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን  ዋና አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ደቻሳ በዞናቸው አሙሩ ወረዳ የጸጥታ ችግር ተፈጥሮ እንደነበር ገልጸው ነበር። በቤኒሻንጉል ክልል መተከል ዞን ቡሌን ወረዳ ደግሞ ትናንት እና ዛሬ ሁለት ሰዎች ህይወት በታጣቂዎች ሲያልፍ አምስትሰዎች ደግሞ በጸጥታ ኃይሎች ትናንት መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱላዚም መሀመድ በመተከል ዞን ያለውን ችግር ከኮማንድ ፖስቱ ጋር ለመፍታት እየሠሩ እንደሚገኙ ገልጸው የክልሉ የቀድሞ ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩ ኮማንደር ፈረደ ቦጅ ከትናንት በስቲያ በአሶሳ ዞን ኦዳ ብልድግሉ በተባለ ወረዳ ውስጥ በታጣቂዎች መገደላቸውንም አክለዋል።

ነጋሳ ደሳለኝ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ