1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቤንሻንጉል የቀጠለው የተቃዋሚ መሪዎች እስር

ማክሰኞ፣ ጥር 12 2012

የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ አብዱል ሰላም ሸንግል እና የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ግራኝ ጉዴታ አሶሳ ውስጥ ታሰሩ። የቤኒሻንል ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ የሕዝብ ግንኘነት ኃላፊ አቶ መሀመድ እስማኤል ሁለቱ የፖለቲካ የድርጀት መሪዎች በፖሊስ የታሰሩት ትናንት ሰኞ መኾኑን ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3WaKe
Asosa, West-Äthiopien und Hauptstadt der Region Benishangul-Gumuz
ምስል privat

የታሰሩት የሁለት ፓርቲዎች ሊቀመናብርት ነበሩ

የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ አብዱል ሰላም ሸንግል እና የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ግራኝ ጉዴታ አሶሳ ውስጥ ታሰሩ። የቤኒሻንል ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ የሕዝብ ግንኘነት ኃላፊ አቶ መሀመድ እስማኤል ሁለቱ የፖለቲካ የድርጀት መሪዎች በፖሊስ የታሰሩት ትናንት ሰኞ መኾኑን ለዶይቸ ቬለ (DW) ተናግረዋል። ሁለቱ ደርጅቶች ባለፈው ሳምንት የጋራ ጉባኤ አዘጋጅተው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲዊ ግንባር የሚል ጥምረት መመስረታቸውንም አቶ መሐመድ ገልጸዋል። ከጋራ ጉባኤው በፊት ግን ሁለቱ ፓርቲዎች ላይ ቀደም ሲል ተደጋጋሚ ዛቻዎች ይደርሱባቸው እንደነበርም አክለው ተናግረዋል። የክልሉ ባለሥልጣናት ፖለቲከኞቹ የታሰሩት በወንጀል ተጠርጥረው ነው ብለዋል።  

የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ አብዱል ሰላም ሸንግልና የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ግራኝን ጉዴታ ትናንት ከመኖረያ ቤታቸው ተይዘው መታሰራቸውን የቤኒሻንል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ መሐመድ እስማኤል  ተናግረዋል፡፡ የድርጅታቸው ሊቀመንበር አቶ አብዱል ሰለም ሸንገልና የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲዊ ንቅናቄ ሊቀመንር አቶ ግራኝ ጉዴታ እስራት የተለመደው የክልሉ መንግስት የህዝቦች ድምጽ የማፈን ተግባር ነው ብለዋል አቶ መሐመድ፡፡ ሁለቱ የፖለቲካ ድርጅቶት ባለፈው ሳምንት የጋራ ጉባኤ ያካሄዱ ሲሆን ጉባኤ ከማካሄዳው ቸው አስቀድሞ ውይይቶችን እንዳያደረጉ የተለያዩ ዛቻዎች ሲደርባቸው እንደነበር ገልጸዋል፡፡  የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄና የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ባለፈው ቅዳሜና እሁድ ጉባኤ ካካሄዱ በኃላ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር የሚል ጥምረት መመስረታውን አቶ መሐመድ ተናግረዋል፡፡ ሁለቱ ድርጅቶች በፈጠሩኑት ግንባርም አቶ አብዱልሰላም ሸንጉል የጅርጅቱ ሊቀመንበር ሲሆኑ አቶ ግራኝ ጉዴታ ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው መሰየማቸውን ጠቁመዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሠላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አበራ ባያታ የታሰሩት በወንጀል ተጠርጠረው ነው ብለዋል፡፡  የታሰሩበት ምክንያት ለጊዜው በፖሊስ እየጠጣራ በመሆኑም መረጃ እንደለላቸው ግልተዋል፡፡ የለንም ብለዋል፡፡ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መሀመድ አምደኒል መረጃ ለማግኘት በተደጋጋሚ በስልክ ያደረኩት ሙከራ ስልክ ባለማንሳቸው አልተሳካም፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር በበኩላቸው አቶ ግራን ጉዴታ የሚመሩት የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) በአንድ አንድ የክልሉ አካባቢዎች የመንግስትን መዋቅር በማፍረስ የራሱን አደረጃጀት እያወቀረ በመሆኑ መንግስት እርምጃ ይሰወዳል ብለዋል፡፡ ሁለቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ከስድስት ዓመት በፊት በምርጫ ቦርድ የተመዘገቡና ዕውቅና ያገኙ ሲሆን በ2007 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫም ተሳትፈው ነበር፡፡

ነጋሣ ደሳለኝ 


ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ