1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቤኒሻንጉል ጸረ ሰላም ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ መባሉ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 3 2014

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ሸርቆለ ወረዳ ጸረ ሰላም በተባሉ ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡ በወረዳው በተደረገው አሰሳ 23 በሚደርሱ ጸረ ሰላም በተባሉ ኃይሎች ላይ እርምጃ መወሰዱንና 5ቱን ደግሞ መማረካቸውን የክልሉ ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ገልጸዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4FK2B
Äthiopien Benishangul Gumuz startet Satellitenfernsehen
ምስል Negessa Dessalegn/DW

በቤኒሻንጉል አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ  ክልል አሶሳ ዞን ሸርቆለ ወረዳ ጸረ ሰላም በተባሉ ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡ በወረዳው በተደረገው አሰሳ 23 በሚደርሱ ጸረ ሰላም በተባሉ ኃይሎች ላይ እርምጃ መወሰዱንና 5ቱን ደግሞ መማረካቸውን የክልሉ ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ  ቢሮ ገልጸዋል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሠላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሳ ሀሚድ እንደተናገሩት በወረዳው የፌደራል እና የክልሉ ፖሊስ በጥምር ኦፕሬሽን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በተወሰደው እርምጃ በርካቶች ወደ ሱዳን መሸሻቸውን አቶ ሙሳ ተናግረዋል፡፡ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱት የቤ.ህ.ነ.ን ታጣቂዎች መሆናቸውን ጠቅሶ በክልሉ ከተወሰኑ ወረዳዎች ውጪ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን አክለዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ በበኩሉ ከታጣቂዎቹ ጋር ግንኙነት እንደለለው አስታውቋል፡፡  የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት  በክልሉ የሚንቀሳቀሱ 1826 ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ባወጣው መግለጫ ገልጸዋል፡፡

ከአሶሳ ከተማ በ98 ኪ፣ሜ ርቀት ላይ በሚትገኘው ሸርቆሌ የተባለች ወረዳ ውስጥ የወርቅ ማውጫ ስፍራን ለመቆጣጠርና ሁኬት ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ጸረ ሰላም የተባሉ ሀይሎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ መንግስት አመልክተዋል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሳ ሀሚድ  በሱዳን ውስጥ ሲሰለጥኑ ነበር ያሏቸው ሀይሎች ከአራት ጊዜ በላይ በአካባቢው ጥቃት ለመፈጸም ሲሞክሩ ነበር ብሏል፡፡ የሀገር መካከላከያ እና የክልል ጸጥታ ሀይሎች በጋራ በወሰዱት እርምጃ ከተደመሰሱት በተጨማሪ ምግብ እና ቁሳቁስ ሰያቀብሉ ነበር የተባሉ 30 የሚደርሱት በቁጥጥር ስር  መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡ በአካባቢው የሚንቀሳቁት ሀይሎች የቤ.ህ.ነ.ን ታጣቂዎች እንደሆኑ  አቶ ሙሳ የተናገሩ ሲሆን በርካታ የጦር መሳሪያዎች  ከታጣቂዎች ጋር መያዛቸውንም አክለዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ(ቤ.ህ.ነ.ን) የፖለቲካ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መሐመድ ኢስማኤል በበኩላቸው ፓርቲአቸው በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ በህጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በጠረፋማ አካባቢዎች ይንቀሳቀሰሉ የተባሉ ታጣቂዎችም ከፓርቲአቸው ጋር የማይገናኙ መሆኑን ለዶይቼቨለ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ፓርቲው ከታጣቂ ቡድኖች ጋር ግንኙነት እንደለለው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ጨምሮ ለክልሉ መንግስትም ማሳወቃቸውን አቶ መሐመድ ጠቁመዋል፡፡ ታጣቂዎቹ በራሳቸው መንገድ ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ናቸው ብሏል፡፡

የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ትናንት ባወጣው መግለጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን  ገልጸዋል፡፡ በክልሉ 65  የጠላት ካምፖች መወደማቸውን እና በክልሉ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎችም መደምሰሳቸውን እንዲሁም ከ1 ሺ 8 መቶ በላይ የሚሆኑት ታጣቂዎች ደግሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በመግለጫው ተመላክቷል፡፡ በጠላት እጅ ነበሩ ያላቸው 180 ቀበሌዎች ነጻ መውጣታቸውን በመግለጫው የተጠቀሰ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 169 በሚደርሱት ደግሞ የመንግስት መዋቅር መልሶ መደራጁቱን በመግለጫው ይፋ አድርጓል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ