1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ዝግጅት

ቅዳሜ፣ መጋቢት 18 2013

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ  ለመሳተፍ እንቅሰቀቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኙት  የቤኒሻንጉል  ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ የምርጫ ቅስቀሳ ለማካሄድ የሚያስችላቸውን የምርጫ ስነ ምግባር ስልጠና በሚወዳደርባቸው ወረዳዎች መስጠት መጀመሩን አስታውቋል፡፡

https://p.dw.com/p/3rEN7
Assosa Town Äthiopien
ምስል DW/N. Dessalegn

የፖለቲካ ፓርቲዎች ዝግጅት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ  ለመሳተፍ እንቅሰቀቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኙት  የቤኒሻንጉል  ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ የምርጫ ቅስቀሳ ለማካሄድ የሚያስችላቸውን የምርጫ ስነ ምግባር ስልጠና በሚወዳደርባቸው ወረዳዎች መስጠት መጀመሩን አስታውቋል፡፡ ፓርቲው በአመራሮቹ ላይ ይደርስ በነበረው ጫና ምክንያት ለምርጫ የሚያደርገውን ዝግጅት ዘግይቶ መጀመሩንም የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አብዱል ሰላም ሸንግል ተናግረዋል፡፡ ሌላው ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ እና በመተከል ዞን ሁሉም ወረዳዎች እንደሚወዳደር የገለጸው ቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲው በበኩሉ 25 ዕጩዎችን ለክልል ምክር ቤት አንድ ደግሞ ለህዝብ ተወካዎች ምክር ቤት ማስመዝገቡን ገልጸዋል፡፡ በዞኑ ባለው ጸጥታ ችግር ምክንያት እስካሁን የምርጫ ቅስቀሳ አለመቸመራቸውን የፓርቲው ሀላፊ አቶ ዩሐንስ ተሰማ ነግረውናል፡፡ በክልሉ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ቅሬታን እና  የምርጫ ቅድመ ዝግጅትን በተመለከተ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ ለማግኘት ያደረኩት ጥረት ስልክ ባለማንሳታቸው አልተሳካም፡፡በዘንድሮ ምርጨ ላይ  በቤኒንጉል ጉሙዝ ከሚወዳደሩት ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርዎች መካከል አንዱ የሆነው የቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ  በመተከል ዞን ሰባት ወራዎች እና በአሶሳ ወረዳ እንደሚወዳደር አስታውቋል፡፡ ለክልል ምክር ቤት እና ለህዝብ ተወካዎች ምክር ቤት 26 ዕጩዎችን ማስመዝገቡንም የፓርቲው የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዩሐንስ ተሰማ ለዲዳቢው ተናግረዋል፡፡  ፓርቲው የሚወዳርው አብዛኛው የመተከል ዞን ወረዳዎች በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የሚፈገውን ያህል መንቀሳቀስ አለመቻላቸውንና የምርጫ ቅስቀሳ አለመጀመራቸውን አክለዋል፡፡የቤኒሻጉል ህዝቦች ነጻነት ንቀናቄ በበኩሉ በበሶስት ዞኖች ውስጥ 67 እጩዎችን ማስመዝገቡን የገለጸ ሲሆን በመተከል ዞን አንድ ወረዳ ብቻ እጩ ማስመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡ የቤኒሻጉል ጉሙዝ ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ሊቀ መንበር አቶ አብዱል ሰላም ሸንግል  ፓርቲአቸው እስካሁን የምርጫ ቅስቀሳ ማካሄድ አለመቻሉንም አመልክቷል፡፡የቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲም 99 እጩዎችን ለክልል ምክር ቤት ማስመዝገቡን ገልጸዋል፡፡ የቤኒሻጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ የፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ካሚል ሀሚድ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው ጊዜ ገደብ መሰረት የዕጩ ምዝገባ ስራውን ማጠናቀቃቸውን አብራርተዋል፡፡በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርዎች በመተከል ባለው የጸጥታ ችግር የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አለመቻላቸውን በተመለከተ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ከአካባቢው አስቸካይ ጊዜ አስተዳደር  መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ስልክ ባለማንሳታቸው አልተሳካም፡፡ ከዚህ ቀደም  የአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደሩ አባል የሆኑት ኮሎኔል አሸናፊ ኦሊ በዞኑ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በተደረገው ጥረት 80ሺ የሚደርሱ ዜጎችን ከጫካ ወደ ቀአቸው መመለሳቸውንና በቀጣይ ደግሞ በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ወደ  ዜጎችን  ለመመለስ  አቅድው እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡በ6ኛ ሀገራዊ ምርጫ ላይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ከሶስት በላይ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሳተፉ ሲሆን የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነነት ንቅናቄ፣የአማራ ብሐራዊ ንቅናቄ ፣ የቦሮ ዴሚክራቲክ ፓርቲ እና ኢዜማ ይገኙበታል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሐመድ