1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቤኒሻንጉል ወደ መኖርያቸዉ እየተመለሱ የሚገኙት ተፈናቃዮች

ሰኞ፣ ሚያዝያ 9 2015

የቤኒሻጉንል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በክልሉ ተፈናቀለው ከነበሩት ዜጎች መካከል 4 መቶ 28 ሺ ሰዎች ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን አስታወቀ፡፡ በክልሉ በአሁኑ ወቅት 46ሺ የሚደርሱ ዜጎች በአሶሳ እና መተከል ዞን በጊዜያዊ መጠለያ እንደሚገኙ የኮሚሽኑ ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ አስታውቋ፡፡

https://p.dw.com/p/4QBws
Äthiopien Binnenflüchtlinge Waghemira
ምስል Waghemira communication

ተፈናቃዮቹ ወደ ቤታቸዉ ቢመለሱም የምግብና ቁሳቁስ ችግር ገጥሟቸዋል

 

የቤኒሻጉንል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በክልሉ ተፈናቀለው ከነበሩት ዜጎች መካከል 4 መቶ 28 ሺ ሰዎች ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን አስታወቀ፡፡ በክልሉ 475ሺ ዜጎች በተለያዩ ምክንያቶች ተፈናቅለው የቆዩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 46ሺ የሚደርሱ ዜጎች በአሶሳ  እና መተከል ዞን በጊዜያዊ መጠለያ እንደሚገኙ የኮሚሽኑ ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ አስታውቋ፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሚገኙ የተፈናቀሉ ዜጎችን ከባለፈው ዓመት ግንቦት 2014 ዓ.ም አንስቶ ወደ የቀያው መመለስ መጀመራቸውን የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ ተናግረዋል፡፡ በክልሉ ሶስቱም ዞኖች ውስጥ በጊዜያ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ከነበሩት 475ሺ ዜጎች መካከል በአሁኑ ወቅት 46 ሺ የሚሆኑት ብቻ መቅርታቸውን ኃላፊ አብራርተዋል፡፡ በመተከል ዞን 24ሺ ሰዎች በአሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ ወደ 22ሺ የሚሆኑ ዜጎች በመጠለያ ጣቢያ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡ በባምባሲ የሚገኙ አብዛኞቹ ከምእራብ ወለጋ ዞን 3 ወረዳዎች ከባለፈው ዓት ጀምሮ ወደ ክልሉ የተሻገሩ እንደሆኑም አክለዋል፡፡

በካማሺ ዞን ያሶ  ወረዳ ወደ ቀያአቸው  የተመሰሉት አቶ ጋዊ ሙልጌታ በታህሳስ 2015 ዓ.ም ወደ ቤታቸው የተመለሱ ቢሆንም ያላቸው ንብረት በሙሉ በመውደሙ ለችግር መጋለጣቸውን ተናግረዋል፡፡ ይሰጣል የተባለው ሰብአዊ ድጋፍ  ከታህሳስ ወር ወዲህ እንዳልአገኙ ጠቁሟል፡፡

በመተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ተፈቅለው የነበሩት አቶ ሀብታሙ ክፍሌ በበኩላቸው መኖርያ ቤታቸው በመቃጠሉ ወደቀያው ተመልሰው ጊዜያ መጠለያ በመስራት እየኖሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ በአካባቢአቸው ያለው የጸጥታ ሁኔታው መሻሻሉን እንዲሁም አርሶ አደሩ በከፊል በእርሻ ስራ ላይ ተሰማርተው መቆየታቸውን አብራርተዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ወደቀያቸው የተመለሱ የዜጎች በዘላቂነት እስክቋቋሙ ድረስ   ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቋሟል፡፡ ከ40ሺ በላይ ቤቶች ከዚህ ቀደም በነበሩት የጸጥታ ችግሮች ሳቢያ ወድመው እንደነበር ጠቁሟል፡፡

ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ወደ ቤንሻንጉል የተፈናቀሉ የአጎራባች ምእራብ ወለጋ ዞን የተፈናቀሉ ዜጎች ወደየ ወረዳቸው እንዲመለሱ ይደረጋል ተብሏል፡፡ የመንግስት የግል ድርጅችን እንዲሁም ባለ ሀብቶችን በማስተባበር ቤቶችን የመገንባት ስራ እንደሚከናውን ተልጸዋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ