1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቤኒሻንጉል ህግ ማስከበር ስራና የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ

ዓርብ፣ ሐምሌ 22 2014

መሻሻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሐሰን አስታውቁ፡፡ በዚህን ዓመት እስካሁን 157 ጸረ ሠላም የተባሉ ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰዱን እና 791 የሚደርሱት ሀይሎች ደግሞ መማረካቸውን ርዕሰ መስዳድሩ ተናግረዋል፡፡ ርዕሰ መስዳድሩ ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር በተደረገው ጥረት በአብዛኛው ስፋራዎች ሰላም እየሰፈነ ነዉ ብሏል።፡

https://p.dw.com/p/4ErQh
Äthiopien Assosa Benishangul Gumuz Regional Council Treffen
ምስል Negassa Dessalegn/DW

በአብዛኛው ስፋራ ሰላም እየሰፈነ ነዉ

መሻሻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሐሰን አስታውቁ፡፡ በዚህን ዓመት እስካሁን 157 ጸረ ሠላም የተባሉ ሀይሎች   ላይ  እርምጃ መውሰዱን እና 791 የሚደርሱት ሀይሎች ደግሞ  መማረካቸውን ርዕሰ መስዳድሩ ተናግረዋል፡፡ ርዕሰ መስዳድሩ ዛሬ መካሄድ በጀመረው የክልሉ 5ኛ ዓመት 8ኛ የስራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ እንደተናሩት   ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር በተደረገው ጥረት  በአብዛኛው ስፋራዎች ሰላም እየሰፈነ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ 82ሺ 8 መቶ 25 የሚሆኑ ዜጎች ከጫካና የተለያዩ ቦታዎች ወደ ቀድሞ ቀያአቸው መመለሳቸውንም አመልክተዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ በመሆን በርካታ ድሎችን ማስመዝገቡን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሐሰን ተናግረዋል፡፡ በተለያዩ ተቋማት  የተከናወኑ ተግባራትን ያካተተውን የአንድ ዓመት ዘገባ በክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ በመገኘት  ያቀረቡት ርዕሰ መስተዳድሩ በጸጥታ ዘርፍ፣ በግብርና እና ማዕድን ዘርፍ የተሻለ ውጤት መታየቱን አብራርተዋል፡፡ በክልሉ የጸጥታ ችግር በሚስተዋልበት አካባቢዎች ሰላም ከማስከበር ጎን ለጎን የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያአቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል ብሏል፡፡ በጸጥታ ሀይሎች በተወሰደው እርምጃ በአንድ ዓመቱ ውስጥ በገጠራማ ስፍራዎች እና በተለያዩ የክልሉ ወረዳዎች ውስጥ ወጣቶችን ጸረ-ሰላም ለተባሉ ሀይሎች የሚመለምሉ ከ40 በላይ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡ ክልሉ ከሱዳን ጋር በሚዋሰንባቸው ስፍራዎች ህጋዊ ያልሆነ የጦር  መሳሪዎችንና የሰዎች ዝውውር ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር መደረጉም ተገልጸዋል፡፡ በርካታ ህገ ወጥ የጦር መሳርያዎች መያዛቸውም የተነገረ ሲሆን የኤርትራ እና የናይጀሪያ ዜጎችን ጨምሮ ወደ  88 የሚደርሱ ግለሰቦች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በኩል ወደ ሱዳን ለመሻገር ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ለምክር ቤቱ አብራርተዋል፡፡

Äthiopien Assosa Benishangul Gumuz Regional Council Treffen
ምስል Negassa Dessalegn/DW

በክልሉ አንጻራዊ ሰላም በሰፈነባቸው ወረዳዎች የትምህርት፣ ግብርና እና የጤና ተቋማት መደበኛ አገልግሎት ሲሰጡ መቆየታቸውን ለምክር ቤቱ ከቀረበው ሪፖርት ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይሁን እና የጸጥታ ችግር በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች ደግሞ 260 በሚደርሱ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ አለመጀመሩን አቶ አሻድሊ ሐሰን አመልክተዋል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የወርቅ ክምችት ከሚገኝባቸው የኢትዮጵያ ክፍሎች አንዱ ሲሆን በማዕድን ልማት ዘርፍም ዘንድሮ ከፍተኛ ገቢ መሰብሰቡን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናገረዋል፡፡ 23 ኩንታር ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባቱንም አክለዋል፡፡ የግብርና፣ የትምህርት፣የጤና እና ጸጥታ ዘርፍ በርዕሰ መስተዳድሩ ከቀረቡት የክልሉ የአንድ ዓመት ስራ ሪፖርት ውስጥ በስፋት ተካተዋል፡፡ በቀጣይም የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያአቸው መመለስ፣ በክልሉ የሚስተለዋለውን ጸጥታ ችግሮችን መቅረፍና የተስተጓጎሉ መሠረተ ልማቶችን ማስፋፋት በሚሉ ጉዳዩች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ተመላክተዋል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዓመት 8 የስራ ዘመን 14ኛ መደበኛው ጉባኤ እስከ ነበው ዕለት የሚቀጥል ሲሆን የለያዩ ውሳ ኔዎች በምክር ቤቱ ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ