በአሶሳ የታሰሩ ሰዎች ቤተሰቦች አቤቱታ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 6 2012ማስታወቂያ
በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ ከሁለት ወር በፊት ተፈጥሮ በነበረው ግጭት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ክስ ሳይቀርብባቸው እና ያለምንም ጥፋት ታስረው እንደሚገኙ የታሳሪ ቤተሰቦች ተናገሩ፡፡ በወቅቱ በወረዳው በነበረው ግጭት የአስር ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ከ100 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተገልጿል፡፡ አብዛኞቹ ታሳሪዎች አርሶ አደሮች እና የመንግስት ሰራተኞች ሲሆኑ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎችም እንደሚገኙበት ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር ያዕቆብ አልማሙን መረጃን በማጣራት ሂደት የተፈጠሩ ክፍተቶች መኖራቸውን አረጋግጠዋል የምርመራ መዝገቡ እየተጠናቀቀ መሆኑንና በቅርቡ ክስ ይመሰረታል ብለዋል፡፡
ነጋሳ ደሳለኝ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ