በቀድሞው የአምስት ብር ገንዘብ መገበያየት ይቀጥላል
ረቡዕ፣ ኅዳር 23 2013ማስታወቂያ
የአምስት ብር የወረቀት ገንዘብ ላልተወሰነ ጊዜ በነበረበት እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዐስታወቀ። በተለያዩ መገበያያ ቦታዎች የብር ቅያሬ የሦስት ወራት ጊዜ ትናንት መጠናቀቁን ተከትሎ አሮጌው የአምስት ብር የወረቀት ገንዘብን አንቀበልም በማለት በተለያዩ ቦታዎች ንትርኮች እየተስተዋሉ ነው። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የባንኩን ፕሬዚደንት ለማናገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ኾኖም የባንኩ አንድ ከፍተኛ አመራርን በማናገር ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ