በሰንዳፋ ታስረው የነበሩ ጋዜጠኞች ተለቀቁ
ሰኞ፣ ግንቦት 19 2011ማስታወቂያ
ባለፈው አርብ በኦሮሚያ ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው የአሃዱ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ጋዜጠኛ ታምራት አበራ ዛሬ መለቀቁን ጣቢያው አስታውቋል። በሰንዳፋ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረው ታምራት ዛሬ ከሰዓት በኋላ የተለቀቀው ፍርድ ቤት ሳይቀርብ፣ በመታወቂያ ዋስ መሆኑንም ሬድዬ ጣቢያው ገልጿል።
ጋዜጠኛ ታምራት የታሰረው በሰንዳፋ በኬ 02 ፖሊስ ጣቢያ የፖሊስ አባላት ባለፈው አርብ ግንቦት 16 ቀን 2011 ዓ.ም መሆኑን የአሃዱ ሬድዮ ጣቢያ በዛሬው መግለጫው ጠቅሷል። የሰንዳፋ በኬ 02 ፖሊስ ጣቢያ አቃቤ ህግ የአሃዱ ሬድዮ ጣቢያ ስራ አስኪያጅ፣ ምክትል ዋና አዘጋጅ፣ የዜና ክፍል ኃላፊ እና ኤዲተር ከነገ በስቲያ ረቡዕ በጽህፈት ቤቱ ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡ በቃል ማዘዙን ጣቢያው አመልክቷል።
የጋዜጠኛ ታምራትን እስር በተመለከተ የአሃዱ ኤፍ ኤም ባለቤት እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ እሸቱ በላይን አነጋግረናል። በዶይቼ ቬለ (DW) አማካኝነት በሚዘጋጀው ዓመታዊው የግሎባል ሚዲያ ፎረም ላይ ለመካፈል እዚህ ቦን ከተማ የሚገኙት አቶ እሸቱን ስቱዲያችን ጋብዘናቸው ጥያቄዎች አቅርበንላቸዋል። አቶ እሸቱ የሰጡትን ምላሽ እና የዜና ዘገባውን የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ።
ዮሃንስ ገብረእግዚያብሔር
ተስፋለም ወልደየስ
ሸዋዬ ለገሰ